ጌታ ፡ ነው (Geita New) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
አለኝ ፡ ያልኩት ፡ ሁሉ ፡ በንፋስ ፡ ሲወሰድ
ከመከራው ፡ ብዛት ፡ ብቻዬን ፡ ስሰደድ
ተስፋዬ ፡ ተሟጦ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ሳለሁ
እጁን ፡ የዘረጋ ፡ እንግዳ ፡ ሰው ፡ አየሁኝ

አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)

ቀንበር ፡ የከበደኝ ፡ ሸግም ፡ የበዛብኝ
ያየኝ ፡ ሁሉ ፡ የጠላኝ ፡ ወዳጅ ፡ የራቀብኝ
ተረስቼ ፡ ማንም ፡ የት ፡ ደረሰ ፡ አይለኝ
አንድ ፡ ድምጽ ፡ ሰማሁ ፡ ና ፡ ልጄ ፡ የሚለኝ

አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)

የኀጢአት ፡ ባሪያ ፡ ሆኜ ፡ ደስታ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ
ከጭንቀቴ ፡ ብዛት ፡ እኔነቴ ፡ አልቆ
ሌት ፡ ተቀን ፡ ፍራቻ ፡ ኑሮ ፡ ሆኖ ፡ እሮሮ
ሞቶ ፡ ወስዶኝ ፡ ነበር ፡ ኢየሱስ ፡ ባይደርስ ፡ ኖሮ

አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)

ባወራው ፡ ባወራው ፡ አያልቅም ፡ ብናገር
እንዴት ፡ እንዳወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ ከሞት ፡ አገር
እድሜ ፡ ቀጥሎልኝ ፡ እስካሁን ፡ አቆየኝ
ሲዖል ፡ ቤቴ ፡ ነበር ፡ አምላኬ ፡ ባያየኝ

አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)