ኢየሱስ ፡ የዋሁ (Eyesus Yewahu) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ
ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ)
ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲዖል ፡ አዳንከኝ
እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ (፪x)

በቅጣት ፡ አለንጋ ፡ ብዙ ፡ ተገረፍኩኝ
በገዛ ፡ ጥፋቴ ፡ ተጠቃሁ ፡ ቆሰልኩኝ
እየተንገዳገድኩ ፡ አመጻዬ ፡ አስክሮኝ
ገደል ፡ ከቶኝ ፡ ነበር ፡ ባትይዘኝ ፡ ገፍትሮኝ

አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ
ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ)
ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ
እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ

የተፈጠርኩበት ፡ ምክንያቱ ፡ ገብቶኛል
የመዳኔ ፡ ሚስጥር ፡ ተገልጦልኛል
የአንተን ፡ አባትነት ፡ የልጅነቴን ፡ መብት
በነጻ ፡ አገኘሁት ፡ የዘላለሙን ፡ ሀብት

አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ
ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ)
ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ
እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ

ተታልዬ ፡ ኖርኩኝ ፡ ማንነቴ ፡ አባብሎኝ
የመርጥኩት ፡ መንገድ ፡ የሚያዋጣኝ ፡ መስሎኝ
ጊዜያዊው ፡ እርካታ ፡ ዓለም ፡ የምትሰጠው
ላዩ ፡ ቢጣፍጥም ፡ ውስጡ ፡ ግን ፡ መርዝ ፡ አለው

አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ
ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ)
ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ
እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ

እኔ ፡ የአለኝን ፡ አጥቶ ፡ ለሚንከራተተው
ጽድቅ ፡ የኖረው ፡ መስሎት ፡ ለሚመጻደቀው
የውስጥ ፡ አይኑ ፡ በርቶ ፡ ምነው ፡ እውነቱን ፡ ባየ
ለክፋቱ ፡ ስትል ፡ እንደተሰቃየህ

አዝ:- ኢየሱሴዋ ፡ ትሁቱ ፡ ወዳጄ
ጠበቃዬ ፡ ብቸኛ ፡ አማላጄ (ብቸኛ ፡ አማላጄ)
ከዘለዓለም ፡ ቁጣ ፡ ከሲኦል ፡ አዳንከኝ
እኔ ፡ ኃጢያተኛውን ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ (፫x)