በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ (Bersu Telewetkugn) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ
ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x)

ቀድሞ ፡ እንደምኖረው ፡ የሞት ፡ ኑሮ ፡ አልኖርም
ኃጢአት ፡ ለመቃረም ፡ ወደ ፡ ዓለም ፡ አልወርድም
ጥፋት ፡ አያምረኝም ፡ መንፈሱ ፡ ገዝቶኛል
ቅዱስ ፡ ደሙን ፡ ረጭቶብኝ ፡ ቅዱስ ፡ አድርጐኛል

አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ
ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x)

ሁሉን ፡ እርግፍ ፡ አድርጌ ፡ ጠቀመኝ ፡ መምጣቴ
ውዴ ፡ አላሳፈረኝም ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ
አሁን ፡ አያይም ፡ ዓይኔ ፡ ወደ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ
የሰው ፡ እጅ ፡ አላይም ፡ አግኝቻለሁ ፡ አጉራሽ

አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ
ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x)

ጩኸቴን ፡ ይሰማል ፡ ድምጼ ፡ ይናፍቀዋል
አሸናፊው ፡ አምላኬ ፡ ድል ፡ አስለምዶኛል
እምበረከካለሁ ፡ ዛሬም ፡ በጸጋው ፡ ዙፋን ፡ ስር
ሲቀበር ፡ አያለሁ ፡ የተጋባኝ ፡ ችግር

አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ
ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x)

የገዛኝ ፡ ተገዛልኝ ፡ አዛዡ ፡ ሆኛለሁ
ባለማዕረግ ፡ ሆንኩኝ ፡ ስልጣን ፡ አግኝቻለሁ
የመድሃኒቴን ፡ ስም ፡ ስጠራ ፡ መደንገጥ
ልማድ ፡ አድርጐታል ፡ ዲያቢሎስ ፡ መፈርጠጥ

አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ
ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፫x)

ባለዉለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፫x)