ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ (Tsega Efelegalehu) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg


(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ
ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x)

ጉልበቴ ፡ ሳይላላ ፡ ሳይቀንስ ፡ ትጋቴ
በቤትህ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ መሻቴ
ልገስግስ ፡ ወደፊት ፡ እየታደሰ ፡ ኃይሌ
በመክሊቴ ፡ ላትርፍ ፡ ይብዛ ፡ ማገልገሌ

አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ
ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x)

የድል ፡ አድራጊ ፡ ልጅ ፡ ባለ ፡ ድል ፡ አርገኸኝ
ሽንፈታም ፡ ነኝ ፡ እያልኩ ፡ ሳወራ ፡ እንዳልገኝ
የሰራህልኝን ፡ መልካሙን ፡ ሥራህን
እንዳልረሳው ፡ እርዳኝ ፡ ያንን ፡ ውለታህን

አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ
ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x)

ፍጻሜዬን ፡ አሳምር ፡ እንደ ፡ ጅማሬዬ
በመልካም ፡ ይደምደም ፡ በፊትህ ፡ ሩጫዬ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ከአንተ ፡ ለአንተ ፡ ነውና
ይኸው ፡ ክበርብኝ ፡ ዝቅ ፡ ልበልና

አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ
ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x)

ለባዕድ ፡ አልሰጥም ፡ ይህን ፡ ጉብዝናዬን
ወስኛለሁ ፡ አጽናው ፡ ቅዱሱን ፡ ምርጫዬን
ልኑር ፡ እንደ ፡ ቃልህ ፡ ግራ ፡ ቀኙን ፡ ሳላይ
እስካገኝ ፡ ርስቴን ፡ እስክገባ ፡ ሰማይ

አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ
ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x)