ተቀይሯል (Teqeyrual) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg


(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ
አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ
ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)

ትርፉ ፡ ድካም ፡ ሁልጊዜ ፡ እሮሮ
ስቆ ፡ ማልቀስ ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ
እዚም ፡ እዚያም ፡ ደስታ ፡ ለማግኘት
ገላገለኝ ፡ ከመንከራተት

አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ
አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ
ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)

አዋጥቶኛል ፡ እርሱን ፡ ማለቴ
እረፍት ፡ ሆነኝ ፡ ሰላም ፡ ለቤቴ
እጅ ፡ እግሬን ፡ የቆለፈ ፡ ኃጢያቴ
በጣጥሶታል ፡ እስራቴን

አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ
አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ
ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)

ሄድኩኝ ፡ በቃ ፡ ተከትየው
መድኃኒቴን ፡ ወድጄው
ሳልመለስ ፡ ፊቴን ፡ ላላዞር
ወስኛለሁ ፡ በእግሩ ፡ ሥር ፡ መኖር

አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ
አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ
ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)

የቀድሞ ፡ ታሪኬን ፡ ትታችሁ
አውሩት ፡ የዛሬውን ፡ ባካችሁ
እንዴት ፡ እንዳዳነኝ ፡ መስክሩ
ይሄ ፡ ነው ፡ ድንቅና ፡ ተዓምሩ

አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ
አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ
ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)

መላ ፡ ያጣ ፡ የተጨነቀ
ተስፋው ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ያለቀ
ይምጣ ፡ ምላሽ ፡ አለ ፡ ኢየሱስ ፡ ጋር
አለቀልኝ ፡ ያለ ፡ የሰጋ

አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ
አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ
ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)