ሰው ፡ እንደፀና (Sew Endetsena) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg


(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና
አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና
ጉልበቱ ፡ ይክደዋል
ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x)

አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም
ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x)

ለውበትህ ፡ ወደር ፡ የለው (፪x)
በሰማይ ፡ በምድር ፡ መሳይ ፡ የለው (፪x)
ኃይሉ ፡ ከሁሉ ፡ የበረታ (፪x)
የጌቶች ፡ ሁሉ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)
ለማንም ፡ አለ ፡ ሳይረታ (፪x)

አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና
አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና
ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል
ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x)

አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም
ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x)

ብርቱ ፡ ኃያላኖች ፡ ተነሱ (፪x)
ሞት ፡ አይቀርምና ፡ ተረሱ (፪x)
እርጅና ፡ ድካም ፡ የማያውቀው (፪x)
ጥበብ ፡ ዕውቀቱ ፡ የጠለቀው (፪x)
ባለ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና
አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና
ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል
ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x)

አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም
ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x)

የተነሱበትን ፡ ያዋርዳል (፪x)
ትዕቢተኞችን ፡ ይቀጣል (፪x)
የተፈሩትን ፡ የማይፈራ (፪x)
ዓይናቸው ፡ እያየ ፡ አለ ፡ እየሰራ (፪x)
እየናደ ፡ ግዙፉን ፡ ተራራ (፪x)

አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና
አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና
ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል
ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x)

አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም
ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x)

ብቻውን ፡ ተዓምራት ፡ ያደርጋል (፪x)
ያለ ፡ ሠራዊት ፡ ይዋጋል (፪x)
በድል ፡ ላይ ፡ ድልን ፡ እያገኘ (፪x)
ጠላቶቹን ፡ አዋርዶ ፡ እየሸኘ (፪x)
አንድ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የተገኘ (፪x)

አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና
አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና
ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል
ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x)

አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም
ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x)