From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው
የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው
አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል
አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል (፪x)
የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ይሄን ፡ ትሁት
ቢደፋ ፡ አንገቱን ፡ ቀላል ፡ አርገውት
እውር ፡ ሲያበራ ፡ ዲዳ ፡ ሲያናግር
በክፉ ፡ አናት ፡ ላይ ፡ እሳት ፡ ሲጭር
ተደንቀው ፡ አዩት ፡ ኧረ ፡ ይሄስ ፡ ማነው
አውሎ ፡ ንፋሱን ፡ ወጀቡን ፡ የሚያዘው
አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው
የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው
አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል
አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል
ትክክለኛ ፡ ሰራተኛ
ሽንገላ ፡ የሌለበት ፡ እውነተኛ
ሃሰተኞች ፡ ቢያደናብሩ
ቃሉን ፡ በተንኮል ፡ ቢመነዝሩ
ልቡ ፡ አይደነግጥ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ አይፈራ
በአደባባይ ፡ በግልጥ ፡ አለ ፡ እየሰራ
አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው
የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው
አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል
አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል
ያንበረከከ ፡ መተተኞችን
በሰው ፡ ላይ ፡ የሚጫወቱ ፡ ጠንቋዮችን
ጓዛቸውን ፡ ጥለው ፡ ፈረጠጡ
በቁጣው ፡ ጅራፍ ፡ እየተቀጡ
ጌታ ፡ ነን ፡ ያሉ ፡ የታል ፡ አቅማቸው
ወድቀው ፡ ቀሩ ፡ እንጂ ፡ ሲነሱ ፡ አላየናቸው
አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው
የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው
አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል
አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል
ወረት ፡ መስሏቸው ፡ የነገራቸው
በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ እነሳለሁ ፡ ሲላቸው
መሳቂያ ፡ አደረጉት ፡ መሳለቂያ
ምን ፡ ልታመጣ ፡ ከእንግዲህ ፡ ወዲያ
የጠበቃት ፡ ቀን ፡ ደረሰችና
አናወጣቸው ፡ ከሞት ፡ ተነሳና
አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው
የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው
አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል
አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል (፪x)
|