ከወደደ ፡ አይለቅም (Kewedede Ayleqem) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg


(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ
ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x)

ስራብ ፡ እያበላኝ ፡ ስጠማ ፡ እያጠጣኝ
ጉዴን ፡ ገመናዬን ፡ እየሸፈነልኝ
ምን ፡ ጐደለህ ፡ እያለ ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ያየኛል
የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ፡ ወዶኛል

አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ
ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x)

ልቤን ፡ የጣልኩበት ፡ ተስፋ ፡ የማደርገው
ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ብድራት ፡ ፊቴ ፡ አለ ፡ የተዘጋጀልኝ
ማንም ፡ አይወስደውም ፡ ኢየሱስ ፡ እያለልኝ

አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ
ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x)

እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ ችግሬን ፡ አስረሳኝ
የማይቻለውን ፡ አስችሎ ፡ አሳለፈኝ
ሰላሙ ፡ በዛልኝ ፡ ሃዘኔ ፡ ተረስቷል
በእግዚአብሔር ፡ በአምላኬ ፡ ደስታዬ ፡ ጨምሯል

አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ
ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x)

ከማር ፡ ይልቅ ፡ ጣፍጦ ፡ አየሁት ፡ ኑሮዬን
እጅግ ፡ አከበርኩት ፡ ቸሩ ፡ መድኃኒቴን
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ሁሌ ፡ ያሰማራኛል
የበረከት ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ባርኮኛል

አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ
ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x)