ከሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ይልቅ (Kesew Lejoch Hulu Yeleq) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg


(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝhttps://play.google.com/store/apps/details?id=com.atpc
የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ (፪x)

የበደሌን ፡ ብዛት ፡ አይተህ ፡ አልሄድክም ፡ ፊትህን ፡ አዙረህ
ይቅርታህ ፡ ለእኔም ፡ ደርሶኛል ፡ . (1) . ፡ አስጀምረኸኛል
እራራህልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ለድካሜ ፡ ማረፊያዬ
ለርሃቤ ፡ ነህ ፡ ጥጋቤ ፡ ለጥማቴ ፡ እርካታዬ

አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ
የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ

ሌት ፡ ተቀን ፡ ሥምህን ፡ ስጠራ ፡ ድንቃ ፡ ድንቅህን ፡ ሳወራ
የሰራህልኝን ፡ ተዓምር ፡ ውለታህን ፡ ስመሰክር
ቢመሽ ፡ ቢነጋ ፡ አልሰለችም ፡ ክብሬ ፡ ነህ ፡ አላፍርብህም
ቆርሼ ፡ መብላት ፡ የቻልኩት ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እንጀራ ፡ ያገኘሁት

አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ
የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ

ግራ ፡ ቀኙን ፡ እየማተርኩ ፡ የሚረዳኝ ፡ እየፈለኩ
አንተን ፡ አገኘሁ ፡ መልካሙን ፡ የሚባርክ ፡ ምስኪኑን
ወጣሁኝ ፡ ከምድረበዳ ፡ ለምለም ፡ ደረቁ ፡ ጓዳ
ቀና ፡ ሆነልኝ ፡ መንገዱ ፡ በቃ ፡ ለኑሮ ፡ መሰደዱ

አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ
የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ

እኔን ፡ ደካማውን ፡ መርጠህ ፡ ብልሹነቴን ፡ ለውጠህ
ውዳቂ ፡ የተጣልኩትን ፡ ሰው ፡ ይገርማል ፡ እንዴት ፡ ወደድከው
ይብዛልህ ፡ ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ዝማሬ ፡ ሆታ ፡ ዕልልታዬ
በብዙ ፡ እረፍት ፡ ያሳረፍከው ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ የኮራ ፡ ማነው

አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ
የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ (፪x)