ገና ፡ ብዙ ፡ ክብር (Gena Bezu Keber) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg

(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል
የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል
ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል
ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x)

መድኃኒት ፡ አለ ፡ እናንተ ፡ ጋር ፡ አድኖ ፡ ፈውሶ ፡ የሚያስቀር
መንገዱን ፡ ባካችሁ ፡ አሳዩን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ መግቢያውን ፡ በር
ይሉናል ፡ ይለምኑናል ፡ የሚያቁን ፡ የምናውቃቸው
ተፀይፈው ፡ ያባረሩን ፡ ከሰፈር ፡ ከመንደራቸው

አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል
የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል
ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል
ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x)

የኃጥያት ፡ የችግር ፡ ቀንበር ፡ ተጭኖ ፡ በሰው ፡ ሁሉ ፡ ላይ
መታወቂያችን ፡ ርሃብ ፡ ሆነ ፡ ተንቀናል ፡ ዞሮ ፡ እኛን ፡ ላይ
የድሆችን ፡ ጩኸት ፡ ሰምቶ ፡ ከሰማይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ያወጣል
ቸነፈር ፡ ጉስቁልናውን ፡ አባሮት ፡ ጥጋብ ፡ ይጠራል

አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል
የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል
ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል
ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x)

ከኃጥያት ፡ ጋር ፡ ጨዋታ ፡ ይዘው ፡ በጊዜያዊ ፡ ደስታ ፡ ታለው
ክብራቸውን ፡ በነውር ፡ ሸጠው ፡ ፈጣሪያቸውን ፡ እረስተው
ገለባ ፡ የሚበላ ፡ እሳት ፡ የመለኮት ፡ ኃይል ፡ ይመጣል
አስመሳይ ፡ አታላይ ፡ ሁሉ ፡ ለአንዱ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይሰጣል

አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል
የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል
ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል
ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x)

ፅድቁ ፡ ሊገለጥ ፡ ማዳኑ ፡ ቀረበ ፡ ከትላንት ፡ ዛሬ
የሆታ ፡ ቀን ፡ ሊመጣ ፡ ነው ፡ በምድራችን ፡ ላይ ፡ ዝማሬ
በሥሙ ፡ ድንቅና ፡ ተዓምር ፡ ይሰራል ፡ ዝናው ፡ ይወጣል
በቤት ፡ ጓዳ ፡ በአደባባይ ፡ ኢየሱስ ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡ ይባላል