From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ደባል ፡ አልፈልግም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ አጠጥቶ ፡ አርክቶኛል
የእረፍቴ ፡ ባለቤት ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ
አገዘ ፡ ድካሜን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ (፪x)
ቀንበር ፡ የከበደው ፡ ብዙ ፡ ሸክም ፡ የተጫነው
የሚያሳርፍ ፡ አጥቶ ፡ የባዘነን ፡ እንደኔ ፡ ማነው
የችግር ፡ ቀን ፡ ወዳጅ ፡ ባልንጀራ ፡ ከጐኔ ፡ ጠፍቶ
ደርሶ ፡ የታደገኝ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ ድረስ ፡ መጥቶ
አዝ፦ ደባል ፡ አልፈልግም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ አጠጥቶ ፡ አርክቶኛል
የእረፍቴ ፡ ባለቤት ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ
አገዘ ፡ ድካሜን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ (፪x)
ሁሉን ፡ አሳልፎ ፡ ለቁም ፡ ነገር ፡ እኔን ፡ ሲያበቃ
ክብሩን ፡ ለሌላ ፡ አልሰጥ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ እየረዳኝ
ውርደቴን ፡ ለወጠ ፡ ተራ ፡ ደርሶኝ ፡ አሳረፈኝ
ሜዳ ፡ ተራራውን ፡ ሰርጓጐቱን ፡ አሳለፈኝ
አዝ፦ ደባል ፡ አልፈልግም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ አጠጥቶ ፡ አርክቶኛል
የእረፍቴ ፡ ባለቤት ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ
አገዘ ፡ ድካሜን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ (፪x)
ወዲህ ፡ ወዲያ ፡ አልል ፡ አልቅበዘበዝ ፡ ከእንግዲህማ
ጩኸቴ ፡ በአምላኬ ፡ ልመናዬ ፡ ከተሰማ
መድኃኒቴ ፡ ሆነኝ ፡ ፈውሶኛል ፡ ያለ ፡ ጠባሳ
ቀረ ፡ መጨነቄ ፡ ሄዶልኛል ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ አበሳ
አዝ፦ ደባል ፡ አልፈልግም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ አጠጥቶ ፡ አርክቶኛል
የእረፍቴ ፡ ባለቤት ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ
አገዘ ፡ ድካሜን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ (፪x)
በሌላ ፡ ሲመካ ፡ ባለው ፡ ሃብቱ ፡ ሲንጠራራ
ልቡ ፡ አውቆ ፡ በትዕቢት ፡ በሚጠፋ ፡ በራሱ ፡ ሲኩራራ
የሚመካ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ይመካ ፡ በኃያሉ
ተስፋ ፡ ሰጥቶ ፡ አይክድም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ በቃሉ
አዝ፦ ደባል ፡ አልፈልግም ፡ (ደባል ፡ አልፈልግም)
ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል ፡ (ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል)
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ አጠጥቶ ፡ አርክቶኛል
የእረፍቴ ፡ ባለቤት ፡ (የእረፍቴ ፡ ባለቤት)
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ (የዘለዓለም ፡ ደስታ)
አገዘ ፡ ድካሜን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የእኔ ፡ መከታ (፪x)
|