በሰማይ ፡ እንዳሉ (Besemay Endalu) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Lyrics.jpg


(5)

ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ
(Moten Yereta Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች
እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች
ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ
አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ
አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x)

ሙታን ፡ ሳለን ፡ ያኔ ፡ በደል ፡ የተሞላን
ስንወጋው ፡ ቁስልህን ፡ ኃጥያት ፡ እየሰራን
ፍቅርህ ፡ በርትቶ ፡ ነው ፡ ቁጣህን ፡ የሻረው
ልበ ፡ ቅን ፡ ሆነህ ፡ ነው ፡ ክፉውን ፡ የማርከው (፪x)

አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች
እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች
ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ
አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x)

ተሰበረ ፡ ቀንበር ፡ ሸክም ፡ ተራገፈ
ከእንግዲህ ፡ እስር ፡ የለም ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ አለፈ
ከድካም ፡ በረታን ፡ ጉልበት ፡ አግኝተናል
ኃይልን ፡ በምትሰጠን ፡ ባለ ፡ ድል ፡ ሆነናል (፪x)

አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች
እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች
ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ
አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x)

ከተጠመደብን ፡ ወጥመድ ፡ አስመለጥከን
መኖሪያ ፡ ከለላ ፡ መሸሸጊያ ፡ ሆንከን
ነጣቂም ፡ አይነካን ፡ ምን ፡ ድፍረት ፡ አግኝቶ
ይኸው ፡ ምህረትህን ፡ አይቶ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ በዝቶ (፪x)

አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች
እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች
ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ
አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x)

ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ትከሻ ፡ ስንቱን ፡ አዝሎ ፡ አኑሯል
የአባትነት ፡ ምክርህ ፡ ጠማማን ፡ አቅንቷል
ምን ፡ ያልሆንከው ፡ አለ ፡ ለመረጥከን ፡ ለእኛ
ጉያህ ፡ መግባት ፡ ቻልን ፡ ሆነን ፡ እድለኛ (፪x)

አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች
እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች
እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች
ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ
አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፬x)