From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላቃጠለኝም
በውኃ ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ አልተወኝም
እጁ ፡ እጄን ፡ ይዞታል ፡ አለቀቀኝም
እጁ ፡ እጄን ፡ ይዞታል ፡ አለቀቀኝም (፪x)
ወጀቡን ፡ ተው ፡ አውሎ ፡ ነፋሱንም
እየገሰጸ ፡ ረዳኝ ፡ አልተወኝም
አሻገረኝ ፡ ወዲያ ፡ ወዲያ ፡ ማዶ
አልመሸብኝ ፡ መጥቶልኛል ፡ ማልዶ
አዝ፦ በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላቃጠለኝም
በውኃ ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ አልተወኝም
እጁ ፡ እጄን ፡ ይዞታል ፡ አለቀቀኝም (፪x)
አብሮኝ ፡ ሲጓዝ ፡ ሜዳ ፡ ተራራውን
መቼም ፡ ቢሆን ፡ አልረሳም ፡ ውለታዉን
እያስቻለኝ ፡ ልቤን ፡ እያሰፋ
ደጋገፈኝ ፡ ያዘኝ ፡ እንዳልጠፋ
አዝ፦ በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላቃጠለኝም
በውኃ ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ አልተወኝም
እጁ ፡ እጄን ፡ ይዞታል ፡ አለቀቀኝም (፪x)
አቤት ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ አሳለፈኝ
እየከለለ ፡ ክፉ ፡ እንዳያገኘኝ
ጐኔ ፡ ባይቆም ፡ ለሁለ ፡ ባቄ ፡ ነኝ
ማዕበሉ ፡ ወጀቡ ፡ በከደነኝ
አዝ፦ በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላቃጠለኝም
በውኃ ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ አልተወኝም
እጁ ፡ እጄን ፡ ይዞታል ፡ አለቀቀኝም (፪x)
አይዞህ ፡ ባዬ ፡ አጽናኜ ፡ ጌታዬ
የሰላም ፡ ምንጭ ፡ ደስታዬ ፡ እርካታዬ
ተወጣሁት ፡ ጉልበቴ ፡ ኃይል ፡ ሆኖ
አላፈረም ፡ ማንም ፡ እርሱን ፡ ተማምኖ
አዝ፦ በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላቃጠለኝም
በውኃ ፡ ውስጥ ፡ አልፌ ፡ አላሰጠመኝም
የትናንቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ አልተወኝም
እጁ ፡ እጄን ፡ ይዞታል ፡ አለቀቀኝም (፪x)
|