From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል
ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም
ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም (፪x)
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
የቤት ፡ የጓዳው ፡ መብል ፡ ተሟጦባቸው ፡ ድረስ ፡ ና ፡ ላሉት
በእንባ ፡ በጸሎታቸው ፡ እየጮሁ ፡ ለተማጸኑት
መንገድ ፡ አለው ፡ መላ ፡ በመልሱ ፡ የሚያሳርፍበት
የደረቀውን ፡ ኑሮ ፡ በቸርነቱ ፡ የሚያለመልምበት
አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል
ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም
ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
የቀጠረለትን ፡ ቀን ፡ ምስኪኑን ፡ የሚባርክበት
ይጠብቃል ፡ አውቀን ፡ ምን ፡ እንደተዘጋጀለት
ያያል ፡ እጁ ፡ ሲገባ ፡ ሲያቆምለት ፡ ያን ፡ የደም ፡ እንባ
የሱም ፡ ደሳሳ ፡ ጐጆ ፡ ሰው ፡ በማይንቅ ፡ አምላክ ፡ ታስባ
አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል
ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም
ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
ድንጉጥ ፡ ልበ ፡ ፈሪዎች ፡ ለሰጉ ፡ ለተጠራጣሪዎች
ስለ ፡ ነገ ፡ ተጨንቀው ፡ የትላንቱን ፡ ተዓምር ፡ ለረሱ ፡ ሰዎች
መልዕክት ፡ አለው ፡ ዛሬም ፡ እኔ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ አልተለወጥኩም
ይመስክሩ ፡ ልጆቼ ፡ ተስፋ ፡ ያረጉኝን ፡ አላሳፈርኩም
አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል
ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም
ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
ቀንበር ፡ ለከበዳቸው ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ለመረራቸው
ቀኙን ፡ ግራውን ፡ ቢሉ ፡ ቢንከራተቱ ፡ ላልሞላላቸው
እንጀራ ፡ ላጡ ፡ እንጀራ ፡ ባርኮ ፡ ሰጥቶ ፡ ያቀርባችኋል
ብዙ ፡ ረሃባችሁን ፡ በብዙ ፡ ጥጋብ ፡ ይለውጥላችኋል
አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል
ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም
ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)
|