From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ
ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ
ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፪x)
ከቤት ፡ ከመንደሩ ፡ ከአባቱ ፡ ቤት ፡ ወጣ
ዘሩን ፡ እንደ ፡ አሸዋ ፡ ሊያበዛለት ፡ መጣ
የብዙ ፡ ህዝብ ፡ አባት ፡ በኩር ፡ አደረገው
መሃኑን ፡ አብረሃም ፡ በልጅ ፡ ልጅ ፡ ባረከው (፫x)
አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ
ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ
ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x)
የገዛ ፡ ወንድሞቹ ፡ ለባዕድ ፡ ሰዎች ፡ ሸጡት
በህልሙ ፡ አንዳች ፡ እንዳይሆን ፡ አሳልፈው ፡ ሰጡት
ነገ ፡ ነገን ፡ ወልዶ ፡ እውነቱ ፡ ወጣና
ወድቀው ፡ ሰገዱለት ፡ ዮሴፍ ፡ ተሾመና (፫x)
አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ
ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ
ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x)
የበግ ፡ ጅራት ፡ ሲከተል ፡ ግራገሩ ፡ እረኛ
ንግሥናውን ፡ አያውቅ ፡ መሆኑን ፡ ተረኛ
ውጣ ፡ ውረዱን ፡ አልፎ ፡ በትሩን ፡ በእጁ ፡ ሰጠው
እልፍ ፡ ገዳይ ፡ አምላክ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ አስቀመጠው (፫x)
አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ
ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ
ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x)
አናብስቶች ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ጣሉት ፡ ቀንተውበት
ከፀሎት ፡ ሌላ ፡ ምክኒያት ፡ ሰበብ ፡ አጥተውበት
አልፈቀደላቸውም ፡ እንዲቀለጣጥሙት
የዳንኤልን ፡ አምላክ ፡ ተባለ ፡ አምልኩት (፫x)
አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ
ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ
ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ
አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x)
|