ተስፋዬ (Tesfaye) - ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ
(Biruk Gebretsadiq)


(1)

ምክንያቱ
(Mekneyatu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 3:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Biruk Gebretsadiq)

ተስፋ ፡ አልቆርጥም ፡ እግዚአብሔር ፡ አለኝ
የሚደግፈኝ ፡ ዛሬን ፡ ያቆመኝ
በጨለማ ፡ ብሄድ ፡ እርሱ ፡ ብርሃኔ ፡ ነው
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ

አዝ፡ ፡ ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ፡ ፡ /3

ሃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
አቅሜም ፡ ጉልበቴም ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
ስጋ ፡ እጅግ ፡ ቢደክምም ፡ ፀጋው ፡ ግን ፡ በቂ ፡ ነው
ፈፅሞ ፡ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው

አዝ፡ ፡ ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ፡ ፡ /3

የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ
ዳግመኛ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ ሃይሌን ፡ አድሳለሁ (፪x)

አዝ፡ ፡ ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ፡ ፡ /5