ተናግሮ ፡ አይረሳም (Tenagro Ayeresam) - ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ
(Biruk Gebretsadiq)


(1)

ምክንያቱ
(Mekneyatu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Biruk Gebretsadiq)

እግዚአብሄር ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ይሆናል
አንድም ፡ ሳይቀር ፡ ይፈፀማል
የተናገረውን ፡ ቃሉን ፡ ያስባል
ሰው ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ እንዴት ፡ ይረሳል

አዝ፡ ፡ ተናግሮ ፡ አይረሳም ፡ ተናግሮ ፡ አይረሳም
ከአፉ ፡ የወጣው ፡ በርግጥ ፡ ፡ ይፈፀማል (፪x)

ይሄ ፡ እንዴት ፡ ይሆን ፡ ከቶ ፡ አይባልም
በውኑ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ
ላይጨርስ ፡ እርሱ ፡ አያስጀምርም
የእውነት ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ፈፅሞ ፡ አይዋሽም

አዝ፡ ፡ ተናግሮ ፡ አይረሳም ፡ ተናግሮ ፡ አይረሳም
ከአፉ ፡ የወጣው ፡ በርግጥ ፡ ፡ ይፈፀማል (፪x)