መኖሪያዬ (Menoriyayie) - ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ
(Biruk Gebretsadiq)


(1)

ምክንያቱ
(Mekneyatu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 3:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Biruk Gebretsadiq)

መኖሪያዬ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ ፡ ነው
በክንዶቹ ፡ ጥላ ፡ አርፋለሁ
የሚያስፈራኝ ፡ ሁሉ ፡ ተወግዷል
ህይወቴን ፡ በሰላም ፡ ሞልቶታል (፪x)

አዝ፡ ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም
 ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም
 ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስለው ፡
እግዚአብሔር ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ (፪x)

እንዲህ ፡ ነህ ፡ ተብሎ ፡ ማይገመተው
ከሰው ፡ ልጅ ፡ እጅግ ፡ የላቀ ፡ ከፍም ፡ ያለ ፡ ነው

አዝ፡ ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም
 ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም
 ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x)

የሞተውን ፡ ነገር ፡ ህያው ፡ ነው ፡ የሚለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
ያለቀውን ፡ ነገር ፡ ይሞላል ፡ የሚለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

እረኛውን ፡ አይቶ ፡ ንጉስ ፡ ነህ ፡ የሚለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው/2

አዝ፡ ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም
የለም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም
አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x)