ምክንያቱ (Mekneyatu) - ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ
(Biruk Gebretsadiq)


(1)

ምክንያቱ
(Mekneyatu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Biruk Gebretsadiq)

ባለፍኩበት ፡ በሄድኩበት ፡ በመንገዴ ፡ ሁሉ
ከነበርኩባቸው ፡ አስጨናቂ ፡ ቀኖቼ
ፀጋህ ፡ ምህረትህ ፡ እያገዘኝ
ዛሬን ፡ አደረሰኝ

አዝ፡ ፡ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ዛሬን ፡ ለመድረሴ
ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ (፪x)

ከማህፀን ፡ ገና ፡ ሳለሁ ፡ በስሜ ፡ የጠራኸኝ
ከልጅነቴ ፡ ጀምሮ ፡ መንገድ ፡ የመራኸኝ
ከጥፋት ፡ ጎዳና ፡ ጠበከኝ ፡ ዛሬን ፡ አሳየኸኝ

አዝ፡ ፡ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ዛሬን ፡ ለማየቴ
ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ (፪x)

ከኔ ፡ የሆነ ፡ ከቶ ፡ ምንም ፡ የለም
ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ የሆነው
ከኔ ፡ የሆነ ፡ ከቶ ፡ ምንም ፡ የለም
ሁሉ ፡ ካንተ ፡ ነው ፡ የሆነው

አዝ፡ ፡ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ዛሬን ፡ ለመድረሴ
ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ (፪x)

ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ