From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ነፍሴን ፡ ጨለማ ፡ ውጧት
መግቢያው ፡ መውጫው ፡ ጠፍቷት
ህይወቴ ፡ በሀጥያት ፡ ተዘፍቃ
አዝ፡ ፡ እንኳን ፡ ልጅህ ፡ ልሆን
በቤትህ ፡ ውስጥ ፡ ልኖር
መኖር ፡ ማይገባኝ ፡ ባሪያ ፡ ነበርኩ (፪x)
ከነሀጥያቴ ፡ ወደድከኝ
ከነሀጥያቴ ፡ መረጥከኝ
ልጅህ ፡ አደረከኝ
በማይጠፋው ፡ ፍቅርህ ፡ ለወጥከኝ (፪x)
መንገዴ ፡ ተሳስቶ ፡ እዳን ፡ ተሸክሜ
በፊህ ፡ ለመሆን ፡ እጅጉን ፡ ቆሽሼ
አዝ፡ ፡ እንኳን ፡ ልጅህ ፡ ልሆን
በቤትህ ፡ ውስጥ ፡ ልኖር
መኖር ፡ ማይገባኝ ፡ ባሪያ ፡ ነበርኩ (፪x)
ከነሀጥያቴ ፡ ወደድከኝ
ከነሀጥያቴ ፡ መረጥከኝ
ልጅህ ፡ አደረከኝ
በማይጠፋው ፡ ፍቅርህ ፡ ለወጥከኝ (፪x)
ወዶኛል ፡ አዳነኝ
በምህረቱ ፡ ሰው ፡ አረገኝ
ሞቼ ፡ ሳለሁ ፡ ከፍጥረቴ
ሕያው ፡ ሆንኩኝ ፡ በኢየሱሴ (፪x)
ከነሀጥያቴ ፡ ወደድከኝ
ከነሀጥያቴ ፡ መረጥከኝ
ልጅህ ፡ አደረከኝ
በማይጠፋው ፡ ፍቅርህ ፡ ለወጥከኝ (፪x)
|