እድለኛ ፡ ነኝ (Edelegna Negn) - ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ
(Biruk Gebretsadiq)


(1)

ምክንያቱ
(Mekneyatu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Biruk Gebretsadiq)

አንተን ፡ ካገኘሁበት ፡ ከዛ ፡ እለት ፡ ጀምሮ
ህይወቴ ፡ ተቀየረ ፡ ሆነ ፡ የሰላም ፡ ጉዞ
አንተን ፡ ካገኘሁበት ፡ ከዛ ፡ እለት ፡ ጀምሮ
ህይወቴ ፡ ተቀየረ ፡ ሆነ ፡ የሰላም ፡ ጉዞ

አዝ፡ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ልጅህ ፡ በመሆኔ
እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ያንተ ፡ በመሆኔ (፪x)

ለራሴ ፡ ከማስበው ፡ በላይ ፡ ታስብልኛለህ
የሚያስፈልገኝን ፡ ሁሉ ፡ ቀድመህ ፡ ታዘጋጃለህ
ከእናት ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ አንተ ፡ እጅጉን ፡ ቅርብ ፡ ነህ
በሀዘን ፡ በደስታዬ ፡ ሁልጊዜ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነህ

አዝ፡ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ልጅህ ፡ በመሆኔ
እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ያንተ ፡ በመሆኔ (፪x)


አዝ፡ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ልጅህ ፡ በመሆኔ
እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ያንተ ፡ በመሆኔ (፪x)