ድነናል (Denenal) - ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ
(Biruk Gebretsadiq)


(1)

ምክንያቱ
(Mekneyatu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብሩክ ፡ ገብረጻዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Biruk Gebretsadiq)

በበደል ፡ በሀጥያት ፡ ሙታን ፡ የነበርነው
ከመንግስቱ ፡ ጠፍተን ፡ ተጨንቀን ፡ ላለነው
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ህይወትን ፡ አገኘን
በርግጥ ፡ ሞተን ፡ ነበር ፡ በፀጋው ፡ አዳነን (፪x)

አዝ፡ ፡ ድነናል ፡ ድነናል ፡ በፀጋው ፡ ድነናል ፡ /3

በጠላት ፡ እስራት ፡ በጨለማ ፡ ሆነን
መሄጃው ፡ ጠፍቶብን ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠን ፡ ሳለን
አርነት ፡ ሊያወጣን ፡ ስለኛ ፡ ቆሰለ
ሞታችንን ፡ ሞቶ ፡ በህይወት ፡ አኖረን (፪x)

አዝ፡ ፡ ድነናል ፡ ድነናል ፡ በፀጋው ፡ ድነናል ፡ /3

በርግጥ ፡ ሞተን ፡ ነበር ፡ በጌታ ፡ ድነናል
የዘላለም ፡ ህይወት ፡ በነፃ ፡ አግኝተናል
ክሳችንን ፡ ከኛ ፡ ከኛ ፡ ላይ ፡ ወስዶታል
ማይጠፋውን ፡ ህይወት ፡ በነፃ ፡ አግኝተናል (፪x)