ዝም ፡ አልልም (Zem Alelem) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

Lyrics.jpg


(2)

እርስ ፡ አልቀይርም
(Erese Alekyerem)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

ደስታዬ በዛ የኔማ
ደስታዬ በዛ የኔማ
መንፈስ ቅዱስ የሱስን ሊያከብረው በኔ
ሃይልን ሰጠኝ ለቀረው ዘመኔ /2

ኧረ እኔስ ዝም አልልም ዝም አልልም
ኧረ እኔስ ዝም አልልም ዝም አልልም
አድርጎኝ የወንጌል አርበኛ ዝም አልልም
የየሱስ ምስክር ነኝና ዝም አልልም
ሆኜ የሱ መገኛ ዝም አልልም
ማደሪያው አርጎኛልና ዝም አልልም
በወንጌል አላፍርምና ዝም አልልም
አደራው አለብኝና ዝም አልልም

ወንጌሉን እናገራለሁ
የምስራቹን እሰብከዋለሁ/2

ኧረ እኔስ ዝም አልልም ዝም አልልም...

ወንጌሉን እናገራለሁ...

ብርሃን ከሰማይ ወጣ ጨለማዬን ገፈፈው
ጌታ ሆይ አንተ ማነህ ስል ለካ እየሱሴ ነው
ባህዛብ በነገስታት ፊት ስሜን ትሸከማለህ አለኝ
እኔም በደስታ ተቀብዬ ይኸው እሰብካለሁኝ/2

ወንጌሉን እናገራለሁ
የምስራቹን እሰብከዋለሁ/2

ወንጌሉን ሰብኬ የታሰረው ይፈታል
ወንጌሉን ሰብኬ የታመመው ይፈወሳል
ወንጌሉን ሰብኬ የወደቀው ይነሳል
ወንጌሉን ሰብኬ ያዘነው ይጽናናል

ወንጌሉን እናገራለሁ...