ያንተ ብቻ (Yante Bicha) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

Lyrics.jpg


(2)

Erese Alekyerem
(Erese Alekyerem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 4:37
ጸሐፊ (Writer): ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

ገናናነት ያንተ ብቻ ነው
ትልቅነት ያንተ ብቻ ነው
ፈጣሪነት ያንተ ብቻ ነው
አምላክነት ያንተ ብቻ ነው

አቻ የለህ ወደር የለህ ብቻኛ ነህ/4

እግዚአብሔር አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ከፈጠርከው ፍጡር ማንስ ለመደህ
ከፍጥረት ጅማሬ እስካሁን ድረስ
ያውቀህም የለም የሸመደደህ

አምላክነትህን አመልከዋለሁ
ፈጣሪነትህን አመልከዋለሁ
ገናናነትህን አመልከዋለሁ
ትልቅነትህን አመልከዋለሁ

አመልከዋለሁ/8

አንተ ብቻ እግዚአብሔር ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ኗሪ
አንተ ብቻ እግዚአብሔር ከጥንት ሳትጎል የነገ ፍፃሜ መሪ/2

አንተ ነህ ዘላለማዊ ብቸኛ የሁሉ ፈጣሪ/4

ገናናነት ያንተ ብቻ ነው
ትልቅነት ያንተ ብቻ ነው
ፈጣሪነት ያንተ ብቻ ነው
አምላክነት ያንተ ብቻ ነው

አቻ የለህ ወደር የለህ ብቻኛ ነህ/8