በቃኝ (Bekagne) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

Lyrics.jpg


(2)

እርስ ፡ አልቀይርም
(Erese Alekyerem)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

ነፍሴ እረክታለች ጥጉ ላይ ደርሳለች
የህይወት መሪዋን የሱስን ይዛለች
ነፍሴ እረክታለች ጥጉ ላይ ደርሳለች
የህይወት ዋናዋን የሱስን ይዛለች

በቃኝ (6x)
ምንም አልፈልግም ከእየሱስ ውጪ
ህይወትን የሚሰጥ የሚያረካኝ የለም/2

እየሱስ ቤቴ የገባ ለታ
ተትረፈረፍኩኝ ህይወቴ በዛ
ከራሴ አልፌ ለሌላም ሆንኩኝ
በረከቴ በዝቶ ማካፈል ጀመርኩኝ
ታዲያ ሌላ ሌላ እንዴት አያለሁ
የሚበልጥ ይዣለሁ

ምን አነሰኝ ምን አነሰኝ
ፀጋ ሰቶ ክብር ካለበሰኝ/3

ነፍሴ እረክታለች ጥጉ ላይ ደርሳለች
የህይወት መሪዋን የሱስን ይዛለች
ነፍሴ እረክታለች ጥጉ ላይ ደርሳለች
የህይወት ዋናዋን የሱስን ይዛለች

ዛሬ አሸብርቆ ለምለም ካባ ለብሶ
ነገ እሳት ሊበላው ሊለዋወጥ ደርሶ
በሚያልፈው ነገር አልታለልም
ከንቱ የሆነውን ውስጤ አያልምም
በእጄ ላይ ያልውን አሳንሼ አላይም ፈጽሞ አላቀልም

ምን አነሰኝ ምን አነሰኝ
ፀጋ ሰቶ ክብር ካለበሰኝ/3

በቃኝ (5x)

በቃኝ (6x)
ምንም አልፈልግም ከእየሱስ ውጪ
ህይወትን የሚሰጥ የሚያረካኝ የለም