From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከአልም እስከ አለም ይስማ ይህን ዝና/2
የእየሱስ ደም የህይወቴ መገኛ
የእየሱስ ደም የነፍሴ መገኛ/2
እህህ የዳቢሎስ ቀንበር እህህ ሆኖ በጫንቃዬ
እህህ በሃጥያቴ ብዛት እህህ ጨልሞ ተስፋዬ
እህህ አብ አባት ከላይ እህህ ስለራራልኝ
እህህ አንድ ልጁን ሰቶ እህህ ነፃ አወጣኝ ልጁ አረገኝ
በደሙ ነው በደሙ ነው ስሜ ስሜ የተፃፈው/2
በሰማይ መዝገብ በህይወት መዝገብ
በደሙ ነው ስሜ የተፃፈው/2
በአብ ፊት ለመቆም ምህረት አግኝቻለው
ቅድስተ ቅዱሳን ይኸው ገብቻለው
ሃጥያት የለብኝም የሚከሰኝ የለም
ነፃ ወጥቻለው በፈሰሰልኝ ደም
በሰላም ወጥቼ በሰላም ምገባው
ስለቻልኩ አይደለም ደሙ ከልሎኝ ነው
ነፃ መውጫዬ የእየሱስ ደም
መፈወሻዬ የእየሱስ ደም
በረከቴ የእየሱስ ደም
ነው አለቴ የእየሱስ ደም
ከአልም እስከ አለም ይስማ ይህን ዝና/2
የእየሱስ ደም የህይወቴ መገኛ
የእየሱስ ደም የነፍሴ መገኛ/2
እህህ በነፃነት መኖር እህህ ለናፈቃት ነፍሴ
እህህ ሰው ሆኖ አዳናት እህህ ጌታ እየሱሴ
እህህ በዋጋ ተገዝቶ እህህ አይባልም ዝም
እህህ ሳመልክ ኖራለው እህህ እስከዘላለም ለዘላለም
በደሙ ነው በደሙ ነው ስሜ ስሜ የተፃፈው/2
በሰማይ መዝገብ በህይወት መዝገብ
በደሙ ነው ስሜ የተፃፈው/2
አበቃለት ብሎ ጠላት ጮቤ ሲረግጥ
የተስፋ ቅሪቴ ጎተራው ሲሟጠጥ
ጎብጬ ስንፏቀቅ በውርደት ሸለቆ
በደሙ አውጣኝ ከጠላት ተናጥቆ
ዛሬ በነፃነት እኔ የማመልከው
ክርስቶስ እየሱስ ባፈሰሰው ደም ነው
ነፃ መውጫዬ የእየሱስ ደም
መፈወሻዬ የእየሱስ ደም
በረከቴ የእየሱስ ደም
ነው አለቴ የእየሱስ ደም
በሰማይ መዝገብ በህይወት መዝገብ
በደሙ ነው ስሜ የተፃፈው
በደሙ ነው/4 ስሜ የተፃፈው
|