፩ኛ ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች - ምዕራፍ ፬ (1st Thesallonians - Chapter 4)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


፩፡ እንግዲህ ፡ በቀረውስ ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ልትመላለሱ ፡ እግዚአብሔርንም ፡ ደስ ፡ ልታሰኙ ፡ እንዴት ፡ እንደሚገባችሁ ፡ ከእኛ ፡ ዘንድ ፡ እንደ ፡ ተቀበላችሁ ፥ እናንተ ፡ ደግሞ ፡ እንደምትመላለሱ ፥ ከፊት ፡ ይልቅ ፡ ትበዙ ፡ ዘንድ ፡ በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ እንለምናችኋለን ፡ እንመክራችሁማለን። ፪፡ በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ የትኛውን ፡ ትእዛዝ ፡ እንደ ፡ ሰጠናችሁ ፡ ታውቃላችሁና። ፫፡ ይህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ እርሱም ፡ መቀደሳችሁ ፡ ነውና ፤ ፬፡ ከዝሙት ፡ እንድትርቁ ፥ እግዚአብሔርን ፡ እንደማያውቁ ፡ አሕዛብ ፡ በፍትወት ፡ ምኞት ፡ አይደለም ፡ እንጂ ፥ ከእናንተ ፡ እያንዳንዱ ፡ የራሱን ፡ ዕቃ ፡ በቅድስናና ፡ በክብር ፡ ያገኝ ፡ ዘንድ ፡ እንዲያውቅ ፤ ፭፡ አስቀድመን ፡ ደግሞ ፡ እንዳልናችሁና ፡ እንደ ፡ መሰከርንላችሁ ፥ ጌታ ፡ ስለዚህ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ የሚበቀል ፡ ነውና ፡ ማንም ፡ በዚህ ፡ ነገር ፡ አይተላለፍ ፡ ወንድሙንም ፡ አያታልል። ፮፡ ለርኵሰት ፡ ሳይሆን ፡ እግዚአብሔር ፡ በቅድስና ፡ ጠርቶናልና። ፯፡ እንግዲህ ፡ የሚጥል ፡ ሰውን ፡ የጣለ ፡ አይደለም ፥ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ በእናንተ ፡ እንዲኖር ፡ የሰጠውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ነው ፡ እንጂ። ፰፡ እናንተ ፡ ራሳችሁ ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ ልትዋደዱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተምራችኋልና ፡ ስለ ፡ ወንድማማች ፡ መዋደድ ፡ ማንም ፡ ይጽፍላችሁ ፡ ዘንድ ፡ አያስፈልጋችሁም ፤ ፱፡ እንዲሁ ፡ በመቄዶንያ ፡ ሁሉ ፡ ላሉት ፡ ወንድሞች ፡ ሁሉ ፡ ታደርጋላችሁና። ነገር ፡ ግን ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ከፊት ፡ ይልቅ ፡ ልትበዙ ፥ በጸጥታም ፡ ትኖሩ ፡ ዘንድ ፡ ልትቀኑ ፥ የራሳችሁንም ፡ ጉዳይ ፡ ልትጠነቀቁ ፥ እንዳዘዝናችሁም ፥ በውጭ ፡ ባሉት ፡ ዘንድ ፡ በአገባብ ፡ እንድትመላለሱ ፥ አንዳችም ፡ እንዳያስፈልጋችሁ ፡ በእጃችሁ ፡ ልትሠሩ ፡ እንለምናችኋለን። ፲፡ ነገር ፡ ግን ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ተስፋ ፡ እንደሌላቸው ፡ እንደ ፡ ሌሎች ፡ ደግሞ ፡ እንዳታዝኑ ፥ አንቀላፍተው ፡ ስላሉቱ ፡ ታውቁ ፡ ዘንድ ፡ እንወዳለን። ፲፩፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ ሞተና ፡ እንደ ፡ ተነሣ ፡ ካመንን ፥ እንዲሁም ፡ በኢየሱስ ፡ ያንቀላፉቱን ፡ እግዚአብሔር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ያመጣቸዋልና። ፲፪፡ በጌታ ፡ ቃል ፡ የምንላችሁ ፡ ይህ ፡ ነውና ፤ እኛ ፡ ሕያዋን ፡ ሆነን ፡ ጌታ ፡ እስኪመጣ ፡ ድረስ ፡ የምንቀር ፡ ያንቀላፉቱን ፡ አንቀድምም ፤ ፲፫፡ ጌታ ፡ ራሱ ፡ በትእዛዝ ፡ በመላእክትም ፡ አለቃ ፡ ድምፅ ፡ በእግዚአብሔርም ፡ መለከት ፡ ከሰማይ ፡ ይወርዳልና ፥ በክርስቶስም ፡ የሞቱ ፡ አስቀድመው ፡ ይነሣሉ ፤ ፲፬፡ ከዚያም ፡ በኋላ ፡ እኛ ፡ ሕያዋን ፡ ሆነን ፡ የምንቀረው ፥ ጌታን ፡ በአየር ፡ ለመቀበል ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ በደመና ፡ እንነጠቃለን ፤ እንዲሁም ፡ ሁልጊዜ ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ እንሆናለን። ፲፭፡ ስለዚህ ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ።














Navigation menu

MediaWiki spam blocked by CleanTalk.