Bezu Mulugeta/Kamlakachen Beqer Manew Amlak/Kamlakachen Beqer

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ብዙ ሙሉጌታ ርዕስ ከአምላካችን በቀር ጸሐፊ ሙሴ

ካምላካችን በቀር ማነው አምላክ ከአለቱስ በቀር ማነው አለት እየሱስ እየሱስ የድል ጋሻ ለክፉቀን ሆነልን መሸሻ ጌታችንን እኛ እናምነዋለን አሸንፎ ባይናችን ስላየን እየሱስን እኛ እናምነዋለን አሸንፎ ባይናችን ስላየን።

ብዙዎች ተነሱ በእርሱ ላይ በስልጣን በሃይሉ በክብሩ ላይ አልጸኑም ወድቀዋል ተገርስሰው በሃያሉ ክንዱ ተመልሰው እኛም ታምነንበት በዚህ ጌታ እንዘላለን ዛሬ በደስታ።


ኦሆ ... እኔ ማመልከው ኦሆ ... የምስግድለት ኦሆ ... የምገዛለት አምላኬ እግዚአብሄር ይሄ ነው።

አማልክቶች አሉ በመደር ላይ ዝናቸው ለጥቂት ገኖ ሚታይ አይጸኑም ይወድቃሉ በአንድ አፍታ ሲነሳ በሃይሉ ይሄ ጌታ ሲያሰግድ አየነው በአይናችን ሕዝቡን ያስከብራል አምላካችን።

አባቶቻችንም ተማምነውት ነብያት ሐዋርያት ስሙን ጠሩት ሰማና ተገኝቶ አሳረፋቸው በጠላት ፊት መፈራት ሆናቸው ጥንት በደንቅ የሰራው ይሄ ጌታ በዙፋኑ አለ ሰይረታ።


እንደ አምላካችን ማነው አለን በስሙ በክንዱ እኛ ፎከርን በመከራው ዘመን ተማመንነው ይሰራል ጌታችን ሃይለኛ ነው ለሁሉም ይሄን ክንዱን አሳያቸው እየሱስ ጌታ ነው አሰኛቸው።