From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ
እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ
እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል
፩) መቃብር ፡ አትሂዱ ፡ የሱስ ፡ በዚያ ፡ የለም
ሕያው ፡ ሆኗል ፡ እሱ ፡ ሕያው ፡ ለዘላለም
እጆቹን ፡ ነክቸ ፡ እኔ ፡ ፈውስ ፡ አገኘሁ
ስለዚህ ፡ ተነስቷል ፡ ተነስቷል ፡ እላለሁ
አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ
እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ
እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል
፪) ዐይኖቸ ፡ አይተውታል ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
በልብ ፡ ጓዳዬ ፡ በኑሮዬ ፡ ገብቷል
አትፍራ ፡ ብሎ ፡ አለኝ ፡ ዳሰኝ ፡ ቅረብና
አዎ ፡ ሕያው ፡ ሆኗል ፡ ኢየሱስ ፡ እንደገና
አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ
እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ
እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል
፫) ዛሬስ ፡ አምሮበታል ፡ ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ
ሁሉን ፡ በመታዘዝ ፡ ስለተቀበለ
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስምም ፡ ተሰጥቶታል
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ የሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ይሉታል
አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ
እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ
እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል
፬) ተስፋ ፡ እንደሌለው ፡ እንበታተንም
ሰብሳቢ ፡ ቃል ፡ አለው ፡ እኛ ፡ አንወድቅም
የሞተ ፡ የማይሰማ ፡ አምላክ ፡ አናመልክም
ይሰራል ፡ ተነስቷል ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ዘላለም
አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ
እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ
እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል
|