የተስፋ ፡ ቃሉን (Yetesfa Qalun) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ
(Bezu Mulugeta)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ አልን! እንደገና
(Eyesus Leyu New Alen Endegena)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፩ (1998)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው
አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ
ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x)
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ምሥጋናችን ፡ ይሄው
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ለኛ ፡ ያደረገው

፩) ተረስተናል ፡ እኛ ፡ አንቅም ፡ ብለን
ጉድጓድ ፡ ለኛ ፡ ጠልቋል ፡ ስንል ፡ አበቃልን
የተስፋ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ የሰጠን ፡ እግዚአብሔር
ባይናችን ፡ አየነው ፡ ሲያወጣን ፡ በክብር (፪x)

አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው
አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ
ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x)
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ምሥጋናችን ፡ ይሄው
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ለኛ ፡ ያደረገው

፪) ጠላት ፡ በሩጫችን ፡ ፍላጻን ፡ ወርውሮ
ያሰብነውን ፡ ስናይ ፡ ሊያስቀረን ፡ ሞክሮ
በሳት ፡ በደመና ፡ የታደገን ፡ ጌታ
ፍላጻን ፡ ሰበረ ፡ ሆነልን ፡ መከታ (፪x)

አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው
አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ
ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x)
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ምሥጋናችን ፡ ይሄው
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ለኛ ፡ ያደረገው

፫) አይችልም ፡ አትበሉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል
ኤልሻዳይነቱን ፡ ታሪክ ፡ ይናገራል
ባሳለፍነው ፡ ጊዜ ፡ እኛም ፡ አይተነዋል
ያለውን ፡ አድራጊ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብለናል (፪x)

የተስፋ ፡ ቃሉን ፡ ፈጸመው

አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው
አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ
ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x)
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ምሥጋናችን ፡ ይሄው
ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ለኛ ፡ ያደረገው