የመከራው ፡ ዘመን (Yemekeraw Zemen) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ
(Bezu Mulugeta)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ አልን! እንደገና
(Eyesus Leyu New Alen Endegena)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፩ (1998)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

የመከራው ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ አለፈና
ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ አልን ፡ እንደገና
ሃሌሉያ ፡ እሰይ ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ አልን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ አሸናፊ ፡ ሆንን (፪x)

ከቁጣው ፡ ጢስ ፡ ወጣ ፡ ፍርድ ፡ ከርሱ ፡ በራ
አሳትም ፡ ነደደ ፡ ከሰማይ ፡ ወጣና
በኪሩቤል ፡ ሆኖ ፡ በፍጥነት ፡ በረረ
የጠላቴን ፡ ሰፈር ፡ ገባ ፡ እየሰበረ (፪x)

ፍላጻውን ፡ ላከ ፡ ሁሉን ፡ በተናቸው
በመብረቁ ፡ እሳት ፡ ጌታ ፡ አወካቸው
ቋጠሮውን ፡ ውሉን ፡ ጌታዬ ፡ ፈታታው
የፎከረን ፡ ጠላት ፡ መደበቂያ ፡ አሳጣው (፪x)

ለወይኔ ፡ አጥር ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ሆኖ
ጠላቴን ፡ በክንዱ ፡ በኃይሉ ፡ በትኖ
ይኸው ፡ ለዚህ ፡ እለት ፡ ልንበቃ ፡ ችለናል
መከራችን ፡ ሁሉ ፡ እንደጉም ፡ ተነስቷል/በኢየሱስ ፡ ተነስቷል