የበግን ፡ መንጋ (Yebegen Menga) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ
(Bezu Mulugeta)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ አልን! እንደገና
(Eyesus Leyu New Alen Endegena)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፩ (1998)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

የበግ ፡ መንጋ ፡ ስጠብቅ
ስሙን ፡ በዜማ ፡ ሳደንቅ
ልዑል ፡ አየና ፡ ከሰማይ
ልቡ ፡ አረፈ ፡ በእኔ ፡ ላይ

እንዴት ፡ ያለ ፡ ዓይን ፡ አለው (፪x)
ከሰው ፡ ልጆች ፡ ልዩ ፡ ነው
ሃሌሉያ (፫x)

ደካማነቴንም ፡ አውቆ
አንበሳውን ፡ ለእኔ ፡ ለቆ
ጠላቴ ፡ ብዙ ፡ ሲሞክር
መጋጋውን ፡ ሰባብሮ

የረዳኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
በዝማሬ ፡ ላመስግነው
ሃሌሉያ (፫x)

ሀይልንም ፡ የሚያስታጥቀኝ
መንገዴንም ፡ የሚያቀና
አጽንቶ ፡ የሚያቆመኝ
ጠላቴንም ፡ የሚረታ

በአማላክት ፡ መካከል
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው
ክብሬ ፡ ትዘምርለት
ማዳኑ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው
ሃሌሉያ (፫x)

በሥጋ ፡ ታናሽ ፡ ብመስልም
ጐልያድ ፡ በእኔ ፡ ቢስቅም
የታመንኩበት ፡ ጌታ ፡ ነው
በጠጠር ፡ የሚዘረጋው

እኩያ ፡ አቻ ፡ የሌለው
ብርቱ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
ሃሌሉያ (፫x)
ተመስገን (፫x)