From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ያለፍነውን ፡ ያሳለፈን ፡ አረማነው
ዮርዳኖስን ፡ የከፈለው ፡ አረ ፡ ማነው
ማነው (፪x) ፡ አረማነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱ ፡ ሃያል
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ኃያል (፪x)
፩) ኃጢአታችን ፡ እጅግ ፡ በዝቶ
ነፍሳችንን ፡ አስጨንቆ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በኛ ፡ አዝኖ
ሀይወታችን ፡ ተበላሽቶ
የተቤዥን ፡ በምህረቱ ፡ ያስታረቀን ፡ ከአባቱ
የዘላለም ፡ ጠባቂያችን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እረኛችን
እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ለዘላለም
የሚችለን ፡ ማንም ፡ የለም
፪) በባዕድ ፡ ምድር ፡ ስንጨቆን
ስንገዛ ፡ በፈርኦን
መከራችን ፡ የተሰማው
ሃዘናችን ፡ ያሳዘነው
እስራትን ፡ የሰበረ ፡ ቀንበሩንም ፡ የሰበረ
ባለድሎች ፡ ያደረገን ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ያጠገበን
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለዘላለም
የሚረዳን ፡ ማንም ፡ የለም
፫) የእኛን ፡ መውደቅ ፡ የተመኙ
ጉድጓዳችንን ፡ የቆፈሩ
በእጃቸው ፡ ተንኮል ፡ ይዘው
ወጥመዶችን ፡ ለእኛ ፡ አጥምደው
ዛሬ ፡ ነገ ፡ ጠፋ ፡ ያለ ፡ የኛን ፡ ረዳት ፡ ያላወቁ
እጃቸውን ፡ በአፋቸው ፡ አድርገዋል ፡ በስራቸው
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለዘላለም
የሚያጸናን ፡ ማንም ፡ የለም
|