ለአንተ ፡ ጌታ (Lante Gieta) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ
(Bezu Mulugeta)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ አልን! እንደገና
(Eyesus Leyu New Alen Endegena)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፩ (1998)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ እና ፡ ወንጌላዊ ፡ ተድላ ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም
ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)

፩) ግራ ፡ ቀኝ ፡ ለሚል ፡ ጭንቀት ፡ ለያዘው
ፈውስን ፡ ፈልጐ ፡ በለቅሶ ፡ ላለው
ደርሶ ፡ የሚፈውስ ፡ የሚታደገው
ሁሉን ፡ የሚችል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም
ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)

፪) በገዢ ፡ ቁጣ ፡ ልቡ ፡ ለራደ
ስፍራውን ፡ ሲለቅ ፡ ሸርተት ፡ ላለ
የንጉሥ ፡ ልቡ ፡ በእጁ ፡ ይሆነው
አጽንቶ ፡ የሚያቆም ፡ መድሃኒያለም ፡ ነው

አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም
ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)

፫) በባዕድ ፡ ምድር ፡ በእስር ፡ ላለ
ተስፋዬ ፡ አሁንስ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ለሚለው
የእስራአኤል ፡ ብርታት ፡ ረዳት ፡ የሆነው
እስረኛን ፡ ፈቺ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም
ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)

፬) በሰማይ ፡ በምድር ፡ የሌለው ፡ መሳይ
ለተዋረደ ፡ ክብርን ፡ የሚያሳይ
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ አረ ፡ ማን ፡ አለ
ሁሉንም ፡ መስራት ፡ ማድረግ ፡ የቻለ

አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም
ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)

፭) እጅህ ፡ ስትሰራ ፡ ማየት ፡ ለጓጓው
ተነስ ፡ እያለ ፡ ፊትህ ፡ ላነባው
በእሳት ፡ መልሰህ ፡ ታሳየዋለህ
ጠላቱን ፡ ጌታ ፡ ታሳፍራለህ

አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም
ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)