From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
፩) ፈርኦን ፡ ሊገዛ ፡ እስራኤልን
ልቡን ፡ አደንድኖ ፡ ከፍ ፡ ቢልም
ሕዝቡን ፡ ለመታደግ ፡ የቆረጠው
የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ አሸነፈው
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
፪) ዳንኤል ፡ ቢጣልም ፡ በጉድጓዱ
አንበሳ ፡ እንዲበላው ፡ ቢታዘዝ
የኃያላን ፡ ሀያል ፡ ኢየሱስ
አዳነ ፡ ካንበሳው ፡ ባሪያውን
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
፫) መከራ ፡ ቢከበን ፡ ዙሪያችን
ተቆረጠ ፡ ስንል ፡ ተስፋችን
በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ የሚል
ልዑል ፡ አምላካችን ፡ ባለድል
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
፬) አይሆንም ፡ ተብሎ ፡ ተቆርጦ
ተስፋዬ ፡ በሙሉ ፡ ተሟጦ
እግዚአብሔር ፡ ቃሉን ፡ አሰበ
ነገር ፡ በጊዜው ፡ ጨኮለ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
፭) አፍ ፡ ባለው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ ብሎ
በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ድንቅ ፡ ሆኖ
የኖረ ፡ ሳይረታ ፡ ዘላለም
እግዚአብሔርን ፡ የሚመስል ፡ የለም
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው
|