From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አሻግረኸናል ፡ ባሕሩን
ከፍለህልናል ፡ ውሃውን
ፈታችን ፡ ሆነህ ፡ ስትመራን
ማንም ፡ አልቻለም ፡ ሊያቆመን
አረ ፡ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ በሰማይ
ማን ፡ ነው ፡ ይፈለግ ፡ የበላይ
ምድርና ፡ ሞላው ፡ ያንተ ፡ ነው
ለሕዝብ ፡ ሞገስ ፡ የሆንከው
ችግራችን ፡ የአንተ ፡ ችግር
ሃዘናችን ፡ የአንተ ፡ ሀዘን
ነበር ፡ ለካ ፡ የኛ ፡ ጌታ
ምትክ ፡ ሆንከን ፡ በኛ ፡ ፈንታ
እስከ ፡ መስቀል ፡ ወደድከን
ከሞት ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ ተሻገርን
ተሸከምነው ፡ የኛን ፡ በደል
፡፡ለዘላለም ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር (፪x)
ስንደክም ፡ ስትበረታ
ስንወድቅ ፡ ሲታገለን
ማን ፡ ነው ፡ እንዳንተ ፡ የቻለን
አለሁ ፡ ያለ ፡ ያልታዬን
ወረት ፡ ከቶ ፡ የማያውቅ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ተባረክ (፬x)
ሆድ ፡ ሲብሰን ፡ ይገባሃል
ብሶታችን ፡ ይሰማሃል
ከስትንፋስ ፡ ይልቅ ፡ ቅርብ ፡ ነህ
ለእኛ ፡ አንተ ፡ ታስባለህ
ከናት ፡ በላይ ፡ አሳዳጊ
ትዕግሥተኛና ፡ አሳላፊ
የተጐዳን ፡ አስታማሚ
ሰው ፡ አድርጐ ፡ ለክብር ፡ ሿሚ
ባሕሩ ፡ ሲቆም ፡ ፊታችን
ፈርኦን ፡ ሲሮጥ ፡ ኋላችን
አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኛ ፡ የደረስክ
ውሃውን ፡ ለሁለት ፡ የከፈልክ
ልባችን ፡ በአንተ ፡ አረፈ
አሳዳጃችን ፡ አፈረ
መርጦናል ፡ ባንተ ፡ መደገፍ
በምንም ፡ ነገር ፡ ብናልፍ
|