From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በወሬ ፡ አይደለም ፡ እኛ ፡ የሰማነው
በሕይወታችን ፡ እልፍ ፡ ጌታ ፡ አደረገው
ልዩ ፡ አፍቃሪ ፡ ወዳጅ ፡ አባት ፡ እግኝተናል
ልናመልክ ፡ ልንሰግድ ፡ በፊቱ ፡ ወጥተናል
ላምልከው ፡ እያልኩኝ ፡ እወደዋለሁኝ
የመስቀሉን ፡ ሚስጥር ፡ ፍቅር ፡ እያየሁኝ
ውለታው ፡ ስለእኔ ፡ እጅግ ፡ በዝቶልናል
እኔ ፡ አበዛለሁ ፡ ለሥሙ ፡ ምስጋና
እርሱ ፡ ብቻ ፡ አምላክ ፡ አባት ፡ ሆኖአልና
ይገባል ፡ ለስሙ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና
ስጡት ፡ ከልባችሁ ፡ አብዙለት ፡ ዘምሩ
ብቻውን ፡ ይመለክ ፡ ይወራለት ፡ ክብሩ
የተነሱበትን ፡ ጥሎ ፡ አዋረዳቸው
ሥልጣኑን ፡ ቀምቶ ፡ ባዶ ፡ አደረጋቸው
እነማን ፡ በርትተው ፡ እግዚአብሔርን ፡ ሻሩ
እርሱ ፡ እኮ ፡ ይኖራል ፡ በነበረ ፡ ክብሩ
፡ ፡ ፡ ሥልጣኑ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነው
፡ ፡ ፡ ፈቅጄ ፡ እመልከዋለሁ
፡ ፡ ፡ ወድጄ ፡ እምበረከካለሁ
፡ ፡ ፡ ልናገር ፡ ከምችለው ፡ በላይ
፡ ፡ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ የክንዱ ፡ ሥልጣን
፡ ፡ ፡ ገብቶኛል ፡ እዘምራለሁ
፡ ፡ ፡ ሥልጣኑ ፡ ከማንም ፡ በላይ ፡ ነው
፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ስልጣኑ
ኃያል ፡ ነን ፡ ጐበዝ ፡ ነን ፡ እያሉ
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ብዙ ፡ ፎረኩ
ታገሰ ፡ ዘመን ፡ ሰጣቸው
ታበዩ ፡ ክንዱ ፡ አጠፋቸው
በዘመኑ ፡ በታሪክ ፡ የለም
ስላጣኑ ፡ ፍፁም ፡ አልተሻረም
እንዴት ፡ ልናወጥ ፡ እንዴትስ ፡ ልፍራ
እያየሁ ፡ የክንዱን ፡ ስራ
ተደላድዬ ፡ ቆሜያለሁ
ኃያሉን ፡ ክንዱን ፡ ይዣለሁ
ሊሰራ ፡ እርሱ ፡ ሲነሳ
እያየሁ ፡ ሁሉም ፡ ይታዘዛል
፡ ፡ ፡ ፡ ፡ስልጣኑ
|