ታስደንቀኛለህ (Tasdeneqegnaleh) - ቤዛ ፡ የአምልኮ ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤዛ ፡ የአምልኮ ፡ አገልግሎት
(Beza Worship Ministry)


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤዛ ፡ የአምልኮ ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Beza Worship Ministry)

ለቁጣ ፡ የዘገየ ፡ ምህረትህ ፡ ለዘለዓለም
ለትውልድ ፡ ትውልድ ፡ የሚያልፍ ፡ ነው ፡ ታማኝነትህ
ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለውም ፡ ማለቂያ ፡ ዳርቻህ
ነፍሴ ፡ ታዜማለች ፡ እንዴት ፡ ግሩም ፡ ነህ

አዝ፦ አንተ ፡ ታስደንቀኛለህ ፡ አንተ (፪x)

አጻሳትም ፡ በስራህ ፡ ፈለግ ፡ የለው ፡ መንገድህ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ከሰው ፡ ዕውቀት ፡ ነው ፡ ጥበብህ
አደራረግህ ፡ እጅግ ፡ ረቂቅ ፡ ፍፁም ፡ ጻድቅ
ነፍሴ ፡ ትቀኛለች ፡ እንዴት ፡ ዕጹብ ፡ ነህ

አዝ፦ አንተ ፡ ታስደንቀኛለህ ፡ አንተ (፪x)

እምባዬን ፡ አብስክ ፡ ፍርሃቴን ፡ አራክ ፡ ኃጢአቴንም ፡ አጠብክ
ዛሬ ፡ ማውቀው ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉም ፡ በሁሉም ፡ ነህ
እምባዬን ፡ አብስክ ፡ ፍርሃቴን ፡ አራክ ፡ ኃጢአቴንም ፡ አጠብክ
ዛሬ ፡ ማውቀው ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዓለሜ ፡ ነህ

አዝ፦ አንተ ፡ ታስደንቀኛለህ (፪x)
(ፍቅር ፣ ሰላም ፣ እረፍት ፣ ቸር ፣ ታጋሽ ፣ መሃሪ)

አዝ፦ አንተ ፡ ታስደንቀኛለህ ፡ አንተ (፬x)

ካየሁህ ፡ ከሰማሁህ ፡ በላይ
ከለመድኩት ፡ በላይ
ሆንክብኝ