ኢየሱስ (Eyesus) - ቤዛ ፡ የአምልኮ ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤዛ ፡ የአምልኮ ፡ አገልግሎት
(Beza Worship Ministry)


(2)

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
(Egziabhier Teleq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤዛ ፡ የአምልኮ ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Beza Worship Ministry)

እንደ ፡ ሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው ፡ ስምህ

በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ መውጫ ፡ መንገድ ፡ ሰላም
ሆኖልኛል ፡ ስምህ ፡ በጭንቅ ፡ ቀን ፡ ድህነት (ኦ)
ነፍሴን ፡ ከሞት ፡ መልሷልና ፡ ከታሰርኩበት ፡ ፈቶኛል
ቀንበሬን ፡ ሰብሮ ፡ ያላየሁትን ፡ ነጻነት ፡ አሳየኝ ፡ ስምህ ፡ ይክበር

አዝ፦ ኦ ፡ ስምህ ፡ ልዩ ፡ ነው
ኦ ፡ እኔም ፡ ወደድኩት
ኦ ፡ ስጠራው ፡ ብውል
ኦ ፡ ከቶ ፡ አልጠግበውም

ከስሞች ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ስምህ
ከሁሉም ፡ ይበልጣል ፡ ኃያል
ኦ ፡ ስጠራው ፡ ብውል
ኦ ፡ ከቶ ፡ አልጠግበውም

ድንቅ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ እሮጦ ፡ ማምለጫ
አላሳፈረኝም ፡ በጭንቀት ፡ ስጠራው
ስምህን ፡ ተማምኖ ፡ የከሰረ ፡ የለም ፡ ኃጢአቱ ፡ ተሽሯል
ኃይሌን ፡ አድሷል ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ በክንፍ ፡ ከፍ ፡ ብያለው ፡ በስምህ ፡ ጉልበት

አዝ፦ ኦ ፡ ስምህ ፡ ልዩ ፡ ነው
ኦ ፡ እኔም ፡ ወደድኩት
ኦ ፡ ስጠራው ፡ ብውል
ኦ ፡ ከቶ ፡ አልጠግበውም

ከስሞች ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ስምህ
ከሁሉም ፡ ይበልጣል ፡ ኃያል
ኦ ፡ ስጠራው ፡ ብውል
ኦ ፡ ከቶ ፡ አልጠግበውም

ድንቅ ፡ መካር ፡ ነው ፡ ልዩ
የሰላም ፡ አለቃ ፡ የዘለዓለም ፡ አባት
ሆሆሆሆ ፡ ሆሆሆሆ
የዘለዓለም ፡ አባት

አዝ፦ ኦ ፡ ስምህ ፡ ልዩ ፡ ነው
ኦ ፡ እኔም ፡ ወደድኩት
ኦ ፡ ስጠራው ፡ ብውል
ኦ ፡ ከቶ ፡ አልጠግበውም (፬x)

ሆ ፡ ሆ ፡ ሆ ፡ ሆ ፡ እኔም ፡ ወደድኩህ