ዘላለማዊ (Zelalemawi) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 3:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ለስምህ ፡ ዘምራለሁ ፡ ምሥጋናህ ፡ በአፌ ፡ ነው
በማለዳ ፡ ምህረትህን ፡ በሌሊትም ፡ እውነትህን ፡ አወራለሁ
በእጣ ፡ ክፍሌ ፡ ስለቆምኩ ፡ በፊትህ ፡ ክብርህን ፡ እንዳወራ
አጥናለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ የመረጥከኝም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለዚህ ፡ ስራ (፪x)

እስካልወሰድክብኝ ፡ እስካለ ፡ እስትንፋሴ ፡ እስካለ ፡ እስትንፋሴ
አቀርብልሃለሁ ፡ የነፍሴን ፡ ውዳሴ ፡ የነፍሴን ፡ ውዳሴ (፪x)

ክበርብኝ ፡ ክበርብኝ
ንገሥብኝ ፡ ንገሥብኝ (፪x)

ዓመታቶችህ ፡ አያልቁምና (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ)
የዕድሜ ፡ መነሻ ፡ መጨረሻ (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ)
የፍጥረት ፡ ንጉሥ ፡ የፍጥረት ፡ ጌታ (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ)
ይሰማ ፡ ለአንተ ፡ በኩር ፡ ምሥጋና (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ) (፪x)

አንተ ፡ ጥንትም ፡ ነበርክ ፡ ዛሬም ፡ አለህ
ለዘላለም ፡ ትኖራለህ ፡ ተከብረህ/ነግሰህ (፬x)