የመኖሬ ፡ ህልውና (Yemenorie Helewena) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

የለኝም ከአንተ በላይ ወዳጅ
የለኝም የኔ ጌታ የለኝም
የለኝም ከአንተ በላይ ረዳት
የለኝም አሄ የለ የለኝም
የሚታደገኝ የሚሸከመኝ የሚራራልኝ የሚያስብልኝ የሚረዳኝ የሚወደኝ
የለኝም ከንተ በላይ የለኝም

ስራዬን ሁሉ የከወነ
ስተት ጉድለቴን አሄ የከደነ
የተሸከምኝ (እስከዛሬ) የሆነኝ ጥላ
እስቲ ማን አለኝ (ለኔ) ከአንተ ሌላ

የመኖሬ ህልውና አንተው ነህ
ከእስትንፋሴ ታስፈልገኛለህ
የመቆሜ ህልውና አንተው ነህ
ከእስትንፋሴ ታስፈልገኛለህ

ነፍሴን በሀይልህ የምታጸናት
ከበጎነትህ አሄ እያጠገብካት
የምትምመራኝ አሄ እረድኤቴ
አንተ አይደለህም ዎይ አቅም ጉልበቴ

የሚታደገኝ የሚሸከመኝ የሚራራልኝ የሚያስብልኝ የሚረዳኝ የሚወደኝ
የለኝም ከንተ በላይ የለኝም

የመኖሬ ህልውና አንተው ነህ
ከእስትንፋሴ ታስፈልገኛለህ
የመቆሜ ህልውና አንተው ነህ
ከእስትንፋሴ ታስፈልገኛለህ

አለኝ አባት አባት
የምመካበት አባት
አለኝ አባት አባት
የምስፈራራበት አባት