የሕይወቴ ፡ ባለቤት (Yehiwotie Balebiet) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 7:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ይሁን ፡ በሚል ፡ ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ሰማያት ፡ ፀኑ
ይሁን ፡ በሚል ፡ ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ይኸው ፡ ዓለሙ
አይተን ፡ የማንጨርሰውን ፡ በእድሜ ፡ ልካችን
ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ ብቻ ፡ አበጀኸልን (፪x)

የስልጣንህ ፡ ቃል ፡ ካፍህ ፡ ሲወጣ
ያልነበረው ፡ ወደ ፡ መኖር ፡ መጣ
ታዘዘ ፡ ሁሉም ፡ ብብልሃትህ
አንተ ፡ እንዳሰብከው ፡ እንዳየህለት (፪x)

ምንጩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መገኛ
ስኖርም ፡ በአንተ ፡ የአንተ ፡ ጥገኛ
ትንፋሼን ፡ እንኳን ፡ ከአንተ ፡ ተውሼ
እንዳከብርበት ፡ አንተን ፡ መልሼ

እኔ ፡ አላውቀውም ፡ የፀጉሬን ፡ ቁጥር
አንተ ፡ ግን ፡ ቆጥረዋለህ
እኔ ፡ አላውቀውም ፡ የዘመኔን ፡ ልክ
አንተ ፡ ለክተኸዋል

እኔማ ፡ በእኔ ፡ አልመጣሁም
እኔን ፡ እኔ ፡ አልመራውም
እኔነቴን ፡ እኔ ፡ አልወሰንኩም
እኔ ፡ የእኔ ፡ አይደለሁም (፪x)

መረጥክለኝ ፡ ትውልድ ፡ ሀገሬን
መረጥክለኝ ፡ ዘሬን ፡ ጐሳዬን
መረጥክልኝ ፡ እናት ፡ አባቴን
መረጥክልኝ ፡ መልኬን ፡ ፆታዬን

ይሁና ፡ አንተ ፡ ያሰብክልኝ
ይሁና ፡ የወደደክልኝ
ይሁና ፡ የመረጥክልኝ
ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁንልኝ (፪x)

አዝ፦ የህይወቴ ፡ ጌታዋ
የህይወቴ ፡ ተጠሪዋ
የህይወቴ ፡ ባለቤት
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በእውነት (፪x)

ስራ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ አረከኝ ፡ እንደማይለው
እኔም ፡ ፍጡር ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የወደደውን ፡ ሚያደርገው
ሸክላ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ አረከኝ ፡ እንደማይለው
እኔም ፡ ፍጡር ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የወደደውን ፡ ሚያደርገው

ስራ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ አረከኝ ፡ እንደማይለው
እኔም ፡ ፍጡር ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የወደደውን ፡ የሚያደርገው
ሸክላ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ መልሰኝ ፡ ቀልሰኝ ፡ አይለውም
ስልጣን ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ እንደወደደ ፡ እንደፈቃዱ ፡ ሊያደርገው

ቢበላሽም ፡ አፍርሶ ፡ እንደገና
ይሰራዋል ፡ ባለቤት ፡ ነዋ
ሸክላ ፡ ሰሪው ፡ ሸክላው ፡ በእጁ ፡ እንዳለ
የእኔም ፡ ህይወት ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ዋለ (፪x)

አዝ፦ የህይወቴ ፡ ጌታዋ
የህይወቴ ፡ ተጠሪዋ
የህይወቴ ፡ ባለቤት
እግዚሀብሄር ፡ ነው ፡ በእውነት (፪x)

እኔማ ፡ በእኔ ፡ አልመጣሁም
እኔን ፡ እኔ ፡ አልመራውም
እኔነቴን ፡ እኔ ፡ አልወሰንኩም
እኔ ፡ የእኔ ፡ አይደለሁም (፪x)

ይሁና ፡ አንተ ፡ ያሰብክልኝ
ይሁና ፡ የወደደክልኝ
ይሁና ፡ የመረጥክልኝ
ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁንልኝ (፪x)