ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን (Tezetayie Qaleh Yehun) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ሕግህን ፡ እጽፈዋለሁ ፡ በልቦናዬ
እንዲሆን ፡ የሞገስ ፡ ዘውዴ ፡ የአንገት ፡ ድርዬ
ሁሌ ፡ ቃልህ ፡ ነውና ፡ የእግሬ ፡ መብራት
መንገዴን ፡ የሚያቀናልኝ ፡ በአንተው ፡ ስርዓት (፪x)

አቤቱ ፡ እንዳልበድልህ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
መንገድም ፡ እንዲነጻልኝ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
በትዕዛዝህ ፡ መንገድ ፡ እንድሮጥ
ተንሸራትቼም ፡ እንዳልገባ ፡ ማጥ
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
ስንፍናን ፡ ተግቼ ፡ ኃጢአትን ፡ ሳላምጥ
ሕይወቴ ፡ በድንገት ፡ እንዳያመልጥ
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን

ስህተትን ፡ እንዳስተውላት ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
እንድሰወር ፡ ከስውር ፡ ኃጢአት ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
ከጓደኞቼ ፡ ጋር ፡ በሳቅ ፡ ጨዋታ
መስመር ፡ እንዳላልፍ ፡ እንዳልረሳ ፡ ጌታ
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
የድፍረት ፡ ኃጢአት ፡ ጠፍሮ ፡ እንዳይዘኝ
የቃልህ ፡ ፍርሃት ፡ ሁልጊዜ ፡ እንዲያዘኝ
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን

ቃልህ ፡ ይሁን ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን (፪x)

መፅናናት ፡ ሲያስፈልገኝ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
መከራው ፡ ሲያሳድደኝ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
ከጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ ከምክሩ ፡ እንዳልፈራ
ልቤ ፡ እንዲጠበቅ ፡ በምክርህ ፡ እንድመራ
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
የኃጥአን ፡ ገመዶች ፡ ሲተበተቡብኝ
አለቆች ፡ ተቀምጠው ፡ ሲያሙኝ
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን

በአመፀኞች ፡ እንዳልቀና ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
የግፍ ፡ እንጀራ ፡ እንዳልበላ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
የጓዳዬን ፡ ኑሮዬን ፡ ቤቴን ፡ ለመሙላት
በከንፈሬ ፡ እንዳልወሰልት
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን
እግሬ ፡ እንዲከለከል ፡ ከክፋት ፡ ጐዳና
በፈተና ፡ ሁሉ ፡ እምነቴ ፡ እንዲፀና
ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን

ቃልህ ፡ ይሁን ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን (፪x)

ሕግህን ፡ እጽፈዋለሁ ፡ በልቦናዬ
እንዲሆን ፡ የሞገስ ፡ ዘውዴ ፡ የአንገት ፡ ድርዬ
ሁሌ ፡ ቃልህ ፡ ነውና ፡ የእግሬ ፡ መብራት
መንገዴን ፡ የሚያቀናልኝ ፡ በአንተው ፡ ስርዓት (፪x)