ጥበበኞችን ፡ ሊያሳፍር (Tebebegnochen Liyasafer) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ሰው ፡ ሰውን ፡ ይወዳል ፡ ይቀርባል ፡ ለጥቅሙ
ቢጤውን ፡ ፈልጐ ፡ እንዳሳቡ
እኔን ፡ ግን ፡ የገረመኝ ፡ የደነቀኝ
እ/ር ፡ ወዶኛል ፡ እንዲሁ ፡ እንዲሁ (፪x)

ተሰማ ፡ ምስራቹ ፡ ሜዳ ፡ ባደሩ ፡ በእረኞቹ
ወንጌሉ ፡ ተሰበከ ፡ ባልተማሩ ፡ ዓሣ ፡ አጥማጆች
ቢሉትም ፡ ግብዞቹ ፡ ያሃጢያተኞች ፡ ዋና ፡ ወዳጅ
እልቀረም ፡ ሳይማርከው ፡ ያንን ፡ ባዩን ፡ ያን ፡ አሳዳጅ
 
ጥበበኞችን ፡ ሊያሳፍር ፡ ያለምን ፡ ደካሞች ፡ መረጠ
የከበሩትን ፡ ሊያሳፍር ፡ ምናምንቴዉን ፡ አከበረ

ይሄው ፡ የዓለም ፡ ቤዛ ፡ ያለም ፡ ንጉስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ እራት ፡ ሊቆርስ ፡ በረከቱን ፡ ሊያፈስስ
ደካሞችን ፡ ሲጠራ ፡ ለእኔም ፡ ደርሶኛል ፡ ጥሪው
ፈልጐ ፡ ከመረጠ ፡ ለምን ፡ አይባል ፡ ምርጫው

ጥበበኞችን ፡ ሊያሳፍር ፡ ያለምን ፡ ደካሞች ፡ መረጠ
የከበሩትን ፡ ሊያሳፍር ፡ ምናምንቴዉን ፡ አከበረ

ጌታን ፡ ሳገለግል ፡ በምን ፡ ጥሩ ፡ ጐኔ
እንዲህ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ፡ እኔ
መረጠኝ ፡ ወደደኝ ፡ ፈለገኝ ፡ መድህኔ
እንዲሁ ፡ እንዲሁ ፡ ከነምኔ ፡ ከነምኔ (፫x)