ረድኤቴ (Redietie) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ዓይኖቼን ፡ አነሳሁ ፡ ወደ ፡ ተራሮቹ
ይረዱኝ ፡ እንደሆን ፡ ብዬ ፡ ትልቆቹ
ታግሼ ፡ ጠበኩኝ ፡ የቃል ፡ ተስፋቸውን
ዛሬ ፡ ነገ ፡ እያልኩኝ ፡ ሳይ ፡ እጅ ፡ እጃቸውን

ክረምት ፡ አልፎ ፡ በጋ ፡ ይኸው ፡ መጣ
ረዳቴ ፡ ግን ፡ ከየት ፡ ከየት ፡ ይምጣ
አቤቱ ፡ ጌታዬ ፡ አድነኝ
በደጅህ ፡ መጣሁኝ ፡ መረጥኩኝ (፪x)

ረድኤቴ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ነው
ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ከሰራው (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ደግ ፡ ነው ፡ አያሳፍርም
ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ አያሳፍርም
የጨለመ ፡ ቢመስልም ፡ አያሳፍርም
ጌታ ፡ ይመጣል ፡ አይቀርም ፡ አያሳፍርም (፪x)

ዓይኖቼን ፡ ቀና ፡ አድርጌ ፡ ያልከኝን ፡ አስታውሳለሁ
መከራዬን ፡ ሀዘኔን ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ እረሳዋለሁ (፪x)

እዛ ፡ ጋር ፡ አለው ፡ ዋጋ (፪x)
አንተ ፡ ጋር ፡ አለው ፡ ዋጋ
እዛ ፡ ጋር ፡ አለው ፡ ዋጋ