በለሲቱን ፡ አትቁረጣት (Belesitun Atquretat) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(4)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:02
ጸሐፊ (Writer): ሩት ሚካኤል
(Ruth Michael
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አንድ ሁለት ቢለው ያ ክፉ በምክሩ
ዘው ብሎ ገባ ቢቀለዉ ነገሩ
ዛሬ ነገን ሲወልድ ቀኑን ቀን ሲገፋ
እዛው ቀጠለበት ልክ እንዳለው ተስፋ

እያዩ አያዩ×2 እየሰሙ አይ
የልቦና አይን ካልበራ እኮ ከላይ

ይኸው ተቀምጧል አለ በእምነት ቤት
መቅረዙ ግን ጠፍቷል የለዉም ዘይት
ማሰብ አይፈልግም ቃሉን በእዉነቱ
ከንቱ መመላለስ ይኸው ነው እምነቱ

እግሩ በእምነት ቤት ቤተኛ
ልቡ ግን ዉጭ ነው አለመኛ ×2

እያሳሳቀች አለም እያባበለች አለም
ጣፋጭ ፍሬዋን አለም እያቀመሰች አለም
ኋላ ግን ኋላ አለም ትተፋሀለች አለም
እንዳትሽር አርጋ አለም ትጥልሀለች አለም
ተለይ ×3 እልፍ በል ተለይ×6
የአምላክህን እቃ የምትሸከም ሆይ

እንድትኖርባት ነው አለምን የሰራት
በእርሷ ዉጣ ግባ ተመላለስባት
እንጂ አትጠላለፍ በክፉ ነገር
የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቄሣር ለቄሣር
ያቃተህን ንገረው ጌታ ቸር ወዳጅ ነው
ስትበረታ ብቻ አይደል የኔ ነህ የሚለው
በትህትናና በተዋረደ በመንፈስ ሆነህ እንዲህ በል
በለሲቱን አትቁረጣት አንድ አመት ታገሳት