በእግዚአብሔር ፡ ምህረት (Begziabhier Meheret) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

የሕይወቴ ፡ ባለቤት
(Yehiwotie Balebiet)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አዝ፦ ለምን ፡ እሩቅ ፡ ልሂድ ፡ ለምን ፡ ጐረቤቴ
ፍቅርህን ፡ ካየሁት ፡ አለሁበት ፡ እኔ
የፍቅርህ ፡ ምሳሌ ፡ የመውደድህ ፡ ምሳሌ
አለሁኝ ፡ እኔ
የማክበርህ ፡ ምሳሌ ፡ የማንሳትህ ፡ ምሳሌ
አለሁኝ ፡ እኔ (፪x)

ምህረትህን ፡ አልከለከልከኝም
በጠላት ፡ እጅ ፡ አልዘጋህብኝም
ሆነህልኝ ፡ የመጠጊያ ፡ ቤቴ
እረሳሁት ፡ ሃዘኔን ፡ ምሬቴን
ተከተለኝ ፡ ቸርነት ፡ ምህረትህ
ጨመረልኝ ፡ የሕይወት ፡ ውበት
በፍቅርህ ፡ ከመደነቅ ፡ በቀር
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሌላ ፡ ነገር

አዝ፦ ለምን ፡ እሩቅ ፡ ልሂድ ፡ ለምን ፡ ጐረቤቴ
ፍቅርህን ፡ ካየሁት ፡ አለሁበት ፡ እኔ
የፍቅርህ ፡ ምሳሌ ፡ የመውደድህ ፡ ምሳሌ
አለሁኝ ፡ እኔ
የማክበርህ ፡ ምሳሌ ፡ የማንሳትህ ፡ ምሳሌ
አለሁኝ ፡ እኔ

ባትመግበኝ ፡ እጅህ ፡ ምህረትህ
እጠፋለሁ ፡ ከዓይንህ ፡ በቅፅበት
የምህረትህ ፡ ጥገኛ ፡ ናት ፡ ነፍሴ
ታስፈልገኛለህ ፡ እንደ ፡ እስትንፋሴ
አዘነብከው ፡ ፍቅርህን ፡ በላዬ
አረሰረሰኝ ፡ ዘልቆ ፡ በጓዳዬ
አያልቅብህ ፡ አንተስ ፡ ደግነት
የትልቅ ፡ የትንሹ ፡ አባት

ይነበብ ፡ ይነበብ ፡ ታሪኬ
ይነገር ፡ በእኔው ፡ አፍ (፪x)
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ተወልጄ
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ታድጌያለሁ
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ሮጬ ፡ ሮጬ
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ እሄዳለሁ (፫x)

በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ተወልጄ
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ታድጌያለሁ
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ሮጬ ፡ ሮጬ
በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ እሄዳለሁ