የሚረባኝን ፡ የሚያውቅልኝ (Yemirebagnen Yemiyawqelegn) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

የሚረባኝን ፡ የሚያውቅልኝ (፪x)
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለኝ
እኔ ፡ ለራሴ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለኝ
እኔ ፡ ለራሴ ፡ አቅምም ፡ የለኝ

አፈርኩበት : እኔ ፡ አውቃለው ፡ ባልኩበት
እኔ ፡ አውቃለው ፡ ባልኩበት
አፈርኩበት ፡ አስቢያለው ፡ ባልኩበት
አውቂያለው ፡ ባልኩበት

አሁንማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
እንግዲማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)

ልጅ ፡ አባቱን ፡ ዳቦ ፡ ቢለው
ድንጋይ ፡ ወስዶ ፡ እንዳይሰጠው
ሰው ፡ መልካምን ፡ ማድረግ ፡ ካወቀ
የእግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ከሰው ፡ የላቅ (፪x)

አሁንማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
እንግዲማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)

አፈርኩበት : እኔ ፡ አውቃለው ፡ ባልኩበት (፪x)
አፈርኩበት ፡ አስቢያለው ፡ ባልኩበት
አውቂያለው ፡ ባልኩበት

ለቀኑ ፡ ክፋቱ ፡ ይበቃዋል
ነገም ፡ ስለ ፡ እራሱ ፡ ይጨነቃል
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው ፡ የሚሆነው
ዝም ፡ ብሎ ፡ የእርሱን ፡ ማዳን ፡ ማየት ፡ ነው

ነፍሴ ፡ አታውኪኝ ፡ አታስጨንቂኝ ፣ ተይ ፡ ተይኝ
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሁንልኝ ፣ ይሁንልኝ (፪x)

ነፍሴ ፡ ልምከርሽ ፡ ቁም ፡ ነገር
እግዚአብሔር ፡ ስለሚወደው ፡ ነገር
ፍቃዴ ፡ ይሁን ፡ ብለሽ ፡ አትደምድሚ
ምን ፡ ይላል ፡ ጌታሽን ፡ ተስማሚ

ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ (፫x)

ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
ተይ ፡ ኧረ ፡ ተይ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ

ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፡ (በምህረቱ : ቸርነቱ : የሚከልልሽ)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ፡ (እንደ ፡ ንስር ፡ የሚያድስ ፡ ቃል ፡ ዋስ ፡ አለብሽ)
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ፡ (ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ፡ (ታመኝዉ ፣ ታመኝዉ)

ተይ ፡ (ታመኝዉ) ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
ተይ ፡ (ታመኝዉ) ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ