From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ በከንቱ ፡ እንዳለፋ ፡ ስለራራልኝ ፡ ስላዘነልኝ
የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አቅጣጫ ፡ አሳየኝ (፪x)
ያየሁትን ፡ መንገድ ፡ ይዤ ፡ እዘልቃለሁ (፪x)
እንደሄድኩም ፡ አልቀር ፡ ዕረፍቴ ፡ እገባለሁ ፡ እገባለሁ (፪x)
ወደ ፡ ዕረፍቴ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ ዕረፍቴ
ወደ ፡ አገሬ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x)
ተስተጓጉዬ ፡ እንዳልቀር ፡ ሜዳ ፡ ላይ
የፊቴን ፡ ትቼ ፡ ግራና ፡ ቀኝ ፡ ሳይ
አሳይቶኛል ፡ አልፎበት ፡ መንገዱን
እከተላለሁ ፡ የርሱን ፡ ፍለጋውን
መንገዴ ፡ ነው ፡ የሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት
ቀና ፡ ምሄድበት ፡ አብ ፡ ጋር ፡ ምደርስበት (፬x)
አዝ፦ በከንቱ ፡ እንዳለፋ ፡ ስለራራልኝ ፡ ስላዘነልኝ
የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አቅጣጫ ፡ አሳየኝ (፪x)
ያየሁትን ፡ መንገድ ፡ ይዤ ፡ እዘልቃለሁ (፪x)
እንደሄድኩም ፡ አልቀር ፡ ዕረፍቴ ፡ እገባለሁ ፡ እገባለሁ (፪x)
ወደ ፡ ዕረፍቴ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ ዕረፍቴ
ወደ ፡ አገሬ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x)
ሰፊው ፡ ጐዳና ፡ አማራጭ ፡ ስላለው
አልመኘውም ፡ ዳርቻው ፡ የሞት ፡ ነው
በጠባቡና ፡ በሕይወት ፡ መንገድ ፡ ላይ
እራመዳለሁ ፡ ተስፋይቷን ፡ እንዳይ
መንገዴ ፡ ነው ፡ የሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት
ቀና ፡ ምሄድበት ፡ አብ ፡ ጋር ፡ ምደርስበት (፬x)
አዝ፦ በከንቱ ፡ እንዳለፋ ፡ ስለራራልኝ ፡ ስላዘነልኝ
የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አቅጣጫ ፡ አሳየኝ (፪x)
ያየሁትን ፡ መንገድ ፡ ይዤ ፡ እዘልቃለሁ (፪x)
እንደሄድኩም ፡ አልቀር ፡ ዕረፍቴ ፡ እገባለሁ ፡ እገባለሁ (፪x)
ወደ ፡ ዕረፍቴ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ ዕረፍቴ
ወደ ፡ አገሬ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x)
|