ተሳልሜ ፡ አልሄድም (Tesalemie Alhiedem) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አነጋልኝ ፡ ዛሬን ፡ በዕድሜዬ ፡ ጨመረው (፪x)
በስሙ ፡ ዋጅቼ ፡ ቀኑን ፡ ልጀምረው (፪x)
አይ ፡ አይ ፡ አይ ፡ አይ
ሳላመልክ ፡ በከንቱ ፡ አይ
አይለፍ ፡ ዕለቱ ፡ አይ ፡ አይ ፡ አይ

አምልኪው ፡ ተብዬ ፡ ተነግሮኝ ፡ ጀምሬ
አምልኩት ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ
አምልኪው ፡ አምልኪው ፡ ተብዬ ፡ ጀምሬ
አምልኩት ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ

እናም ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚመለከው
ጠጋ ፡ ተብሎ ፡ ነው
እንዴ ፡ እግዚአብሐር ፡ የሚመለከው
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ ነው

አዝ፦ ማደሪያው ፡ ስር ፡ እሆናለሁ ፡ እንጂ
ዙፋኑ ፡ ስር ፡ እሰግዳለሁ ፡ እንጂ
ተሳልሜ ፡ አልሄድም ፡ ከደጅ (፬x)

ሃያራቱ ፡ ሽማግሌዎች ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
እልፍ ፡ አእላፍ ፡ መላእክቱ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ምስጋና ፡ አለው ፡ የተረፈ ፡ ከኔ ፡ የሚሻው ፡ ከቃሌ ፡ ባለፈ
አምልኮ ፡ አለው ፡ የተረፈ ፡ እኔም ፡ ልዘምር ፡ ከቃሌ ፡ ባለፈ

ሰው ፡ በከንፈሩ ፡ አምልኮ
ልቡን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ቢያርቀው
ልብን ፡ የሚመረምረው
የአፉን ፡ ቃል ፡ ብቻ ፡ አይሰማው (፪x)

አዝ፦ ማደሪያው ፡ ስር ፡ እሆናለሁ ፡ እንጂ
ዙፋኑ ፡ ስር ፡ እሰግዳለሁ ፡ እንጂ
ተሳልሜ ፡ አልሄድም ፡ ከደጅ (፬x)

ለልቤ ፡ ጌታ ፡ ከልቤ
ለልቤ ፡ ንጉስ ፡ ከልቤ
እስኪ ፡ ልዘምር ፡ ከልቤ
ዛሬም ፡ እንደልጅነቴ (፪x)

እኔ ፡ ያመንኩትን ፡ አውቃለሁኝ ፡ ልንገረው ፡ የሚሻ
እኔ ፡ ያመንኩትን ፡ አውቃለሁኝ ፡ ልንገረው ፡ የሚሻ
ጌታ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ
አምላክ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ (፪x)

ሃይለኛ ፡ የመጀመሪያ ፡ ሃይለኛ ፡ የመጨረሻ
ታዋቂ ፡ የመጀመሪያ ፡ ታዋቂ ፡ የመጨረሻ
ዝነኛ ፡ የመጀመሪያ ፡ ዝነኛ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ
ንጉስ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ ንጉስ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ
ጌታ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ
አምላክ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ